SlideShare uma empresa Scribd logo
1 de 3
SUNSEWA GENERAL CONSTRUCTION & BUSINESS PLC
Page 1
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ሀ”)
ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር
ይከፈልበታል፡፡ቀጣሪ ማለት ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ለተቀጣሪው ደመወዝ የሚከፍል ሰው ወይም ድርጅት ነው ሲሆን ተቀጣሪ ማለት
ደግሞ ራሱን ችሎ የሚሰራን የስራ ተቋራጭ ሳይጨምር በሌላ ሰው /በቀጣሪው/ መሪነትና ቁጥጥር ስር ሆኖ አገልግሎት ለመስጠት በቋሚነት
ወይም በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግለሰብ ሲሆን የድርጅት ዳይሬክተር፣ ወይም በድርጅቱ አመራር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ሌላ ሰው
እንዲሁም ተሿሚንና የህዝብ ተመራጭን ጨምሮ የመንግስት ስራ ኃላፊን ያጠቃልላል፡፡
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-
ከሰራተኛው ቅጥር ጋር በተያያዘ ሰራተኛው የተቀበለው ደመወዝ ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማበረታቻ
ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ክፍያ፣
ሰራተኛው ከቅጥር ውሉ ጋር በተያያዘ በዓይነት የሚቀበለው ማንኛውም ጥቅማጥቅም ዋጋ፣
ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብን ጨምሮ የስራ ውል በመቋረጡ
ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በዳኝነት ውሳኔ መሠረት የተቀበለ ሰው ማንኛውም የገንዘብ መጠን፣
(ሠንጠረዥ “ሀ”) ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር የማስከፈያ ምጣኔዎች
ቀጣሪው ለተቀጣሪው ከተከፈለው የገንዘብ መጠን ላይ ግብሩን ሳይቀንስ ከራሱ ግብሩን የከፈለ እንደሆነ የተከፈለው ግብር
በተቀጣሪው ደመወዝ ላይ ተደምሮ ግበሩ ይሰላል፡፡
በዓይነት ለተቀጣሪው የሚሰጥ ጥቅማጥቅም ዋጋ የሚሰላበትና የሚወሰንበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡
ተ.ቁ የሚገኝ የወር ገቢ በብር ተከፋይ የገቢ ግብር በመቶኛ
1 0 - 600 ነፃ
2 601 – 1650 10
3 1651 - 3200 15
4 3,201 - 5,250 20
5 5,251 - 7,800 25
6 7,801 - 10,900 30
SUNSEWA GENERAL CONSTRUCTION & BUSINESS PLC
Page 2
7 10,900 - በላይ 35
ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ስለመሆን
የሚከተሉት ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ይሆናሉ፡-
ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፣
በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፣
በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፣
ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፣
የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ
ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ
ሀገራቸው ሲመለሱ የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፣
የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፣
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፣
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል
መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፣
ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15 % (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው
የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፣
በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፣
የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ
የሚያገኙት ገቢ፣
በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው
የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡-
ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ
ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ
በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን ወይም በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 135 መሠረት የሚሰጥ ሽልማት፣
በተቀባዩ ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፣
በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፣
በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፣
ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፣
SUNSEWA GENERAL CONSTRUCTION & BUSINESS PLC
Page 3
ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፣
ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ
መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፣
በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፣
ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፣
በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ለኢኮኖሚ፣ ለአስተዳደራዊ ወይም ለማህበራዊ ምክንያቶች አንድን ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ ሊያደርግ
ይችላል፡፡

Mais conteúdo relacionado

Mais de ESHETIE MEKONENE AMARE (20)

Eshetie mekonene research paper
Eshetie mekonene research paperEshetie mekonene research paper
Eshetie mekonene research paper
 
Hiwot aydiko mota/WWW.ESHETIESTU.COM
Hiwot aydiko mota/WWW.ESHETIESTU.COMHiwot aydiko mota/WWW.ESHETIESTU.COM
Hiwot aydiko mota/WWW.ESHETIESTU.COM
 
Revenue from contracts with customers
Revenue from contracts with customersRevenue from contracts with customers
Revenue from contracts with customers
 
New operating segments
New operating segmentsNew operating segments
New operating segments
 
New iias 28
New iias 28New iias 28
New iias 28
 
New ifrs 13 fair value measurment
New ifrs 13 fair value measurmentNew ifrs 13 fair value measurment
New ifrs 13 fair value measurment
 
New ifrs 11 joint arrangements & associates
New ifrs 11 joint arrangements &  associatesNew ifrs 11 joint arrangements &  associates
New ifrs 11 joint arrangements & associates
 
New ifrs 9
New ifrs 9New ifrs 9
New ifrs 9
 
New ias 36
New ias 36New ias 36
New ias 36
 
New ias 21
New ias 21New ias 21
New ias 21
 
New goverment grant ias 20
New goverment grant ias 20New goverment grant ias 20
New goverment grant ias 20
 
New borrowing cost ias 23
New borrowing cost ias 23New borrowing cost ias 23
New borrowing cost ias 23
 
New ias 24 related parties disclosure1
New  ias 24 related parties  disclosure1New  ias 24 related parties  disclosure1
New ias 24 related parties disclosure1
 
Ifrs10
Ifrs10Ifrs10
Ifrs10
 
Ifrs3
Ifrs3Ifrs3
Ifrs3
 
Ifrs 5
Ifrs 5Ifrs 5
Ifrs 5
 
Ifrs 1
Ifrs 1Ifrs 1
Ifrs 1
 
Ias 41-agriculture-summary
Ias 41-agriculture-summaryIas 41-agriculture-summary
Ias 41-agriculture-summary
 
Ias 41-agriculture-summary
Ias 41-agriculture-summaryIas 41-agriculture-summary
Ias 41-agriculture-summary
 
Ias 40
Ias 40Ias 40
Ias 40
 

Amharic version income tax

  • 1. SUNSEWA GENERAL CONSTRUCTION & BUSINESS PLC Page 1 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ሀ”) ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡ቀጣሪ ማለት ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ለተቀጣሪው ደመወዝ የሚከፍል ሰው ወይም ድርጅት ነው ሲሆን ተቀጣሪ ማለት ደግሞ ራሱን ችሎ የሚሰራን የስራ ተቋራጭ ሳይጨምር በሌላ ሰው /በቀጣሪው/ መሪነትና ቁጥጥር ስር ሆኖ አገልግሎት ለመስጠት በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግለሰብ ሲሆን የድርጅት ዳይሬክተር፣ ወይም በድርጅቱ አመራር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ሌላ ሰው እንዲሁም ተሿሚንና የህዝብ ተመራጭን ጨምሮ የመንግስት ስራ ኃላፊን ያጠቃልላል፡፡ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡- ከሰራተኛው ቅጥር ጋር በተያያዘ ሰራተኛው የተቀበለው ደመወዝ ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ክፍያ፣ ሰራተኛው ከቅጥር ውሉ ጋር በተያያዘ በዓይነት የሚቀበለው ማንኛውም ጥቅማጥቅም ዋጋ፣ ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብን ጨምሮ የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በዳኝነት ውሳኔ መሠረት የተቀበለ ሰው ማንኛውም የገንዘብ መጠን፣ (ሠንጠረዥ “ሀ”) ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር የማስከፈያ ምጣኔዎች ቀጣሪው ለተቀጣሪው ከተከፈለው የገንዘብ መጠን ላይ ግብሩን ሳይቀንስ ከራሱ ግብሩን የከፈለ እንደሆነ የተከፈለው ግብር በተቀጣሪው ደመወዝ ላይ ተደምሮ ግበሩ ይሰላል፡፡ በዓይነት ለተቀጣሪው የሚሰጥ ጥቅማጥቅም ዋጋ የሚሰላበትና የሚወሰንበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡ ተ.ቁ የሚገኝ የወር ገቢ በብር ተከፋይ የገቢ ግብር በመቶኛ 1 0 - 600 ነፃ 2 601 – 1650 10 3 1651 - 3200 15 4 3,201 - 5,250 20 5 5,251 - 7,800 25 6 7,801 - 10,900 30
  • 2. SUNSEWA GENERAL CONSTRUCTION & BUSINESS PLC Page 2 7 10,900 - በላይ 35 ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ስለመሆን የሚከተሉት ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ይሆናሉ፡- ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፣ በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፣ በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፣ ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፣ የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፣ የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፣ ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15 % (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፣ በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፣ የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት ገቢ፣ በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፣ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡- ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን ወይም በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 135 መሠረት የሚሰጥ ሽልማት፣ በተቀባዩ ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፣ በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፣ በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፣ ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፣
  • 3. SUNSEWA GENERAL CONSTRUCTION & BUSINESS PLC Page 3 ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፣ ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፣ በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፣ ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፣ በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ለኢኮኖሚ፣ ለአስተዳደራዊ ወይም ለማህበራዊ ምክንያቶች አንድን ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ ሊያደርግ ይችላል፡፡