SlideShare uma empresa Scribd logo
1 de 7
Baixar para ler offline
1 
ሥልጣን በኃይል ለመቀማት ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች የተገለፀ አጋርነት 
ለሚ ዋቄ 
09-08-14 
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በቅርቡ ውጭ ሃገር በሚገኙ ደረ ገፆች አንድ ፅሁፍ አስነብበውናል። “በጥፈሩም በጥርሱም ለሥልጣን የሚተጋ መንግስት እንዴት እንታገለው?” በሚል ርዕሥ የቀረበውን ፅሁፍ መጀመሪያ ስመለከተው የኢፌዴሪ መንግስት ከፍተኛው የሥልጣን አካል የሆነው የህዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት አባል የማይጠበቅ በመሆኑ እርግጥ የተከበሩ አቶ ግርማ ሠይፉ የፃፉት መሆኑን ተጠራጥሬያለሁ። እርግጥ አሁንም አቶ ግርማ በጤናቸው ሆነው የፃፉት ነው የሚል እመነት የለኝም። 
ፅሁፉን አቶ ግርማ ፅፈውትም ይሁን ሌላ ሰው በስማቸው ፅፎት ይዘቱን ስለማይቀይረው የፅሁፉ ይዘት ላይ ላተኩር። በአጠቃላይ ፅሁፉ ከሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ባህርይ ያፈነገጠና ሕገወጥነት ቀመስ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ፃፉት የተባለው ፅሁፍ “. . . መንግስትን በሁሉም አቀፍ ትግል መጣል አለብን ብለው ጠብ መንጃ ቢያነሱ ክፋቱ ምን ላይ እንደሆነ አልታይህ እያለኝ ነው።” በሎ ነው የሚጀምረው። ይህን አቋም እንዲይዙ ያደረጋቸው ደግሞ መንግስት “በጥፍሩም በጥርሱም ለሥልጣን የሚተጋ” በመሆኑ እንደሆነ ነግረውናል። 
የተከበሩ አቶ ግርማ ከላይ የተጠቀሰውን ሃሳብ ሲያሰፍሩ አንድ የዘነጉት ወይም ሆን ብለው የዘለሉት ነገር መኖሩ ይሰማኛል። ይህም ገዢው ፓርቲ ወደ ሥልጣን የመጣው በቸኛ የመንግሥት ሥልጣን ምንጭና ባለቤት በሆነው ሕዝብ የሥልጣን ውክልና ተሰጥቶት መሆኑን ነው። ታዲያ ገዢው ፓርቲ የመንግሥትን ኃላፊነት ሲረከብ ይህን የህዝብ ሥልጣን ከህዝብ ውክልና ውጭ ሥልጣን ለመያዝ ከሚንቀሳቀሱ ቡድኖች በጥፍሩም በጥርሱም ለመጠበቅ መትጋት ይጠበቅበታል። 
ይህን ማደረጉ ከማንኛውም መንግሥት የሚጠበቅና ተገቢ ነው። መንግስት ሕዝብ በውክልና የሰጠውን ሥልጣን፣ ማንኛውም ሥልጣን ናፋቂ ቡድን መንትፎ መውሰድ
2 
እነዲችል እንቅልፋም መሆን የለበትም። ይህን የሚያደርግ ከሆነ መንግስተ የመሆን ብቃት የለውም ማለት ነው። ሥልጣን ከህዝብ በአደራ የሚሰጥ በመሆኑ ከማንኛውም ቀማኛ በጥፍርም በጥርስም መጠበቅ አለበት። ችግር የሚሆነው በጥፍርና በጥርስ መጠበቅ የማይችል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው። 
ከዚህ ጋር ተያይዞ የተከበሩ አቶ ግርማ ሊያስታውሱት የሚገባው ሌላው ጉዳይ የመንግስትን ሥልጣን በጥፍርም በጥርስም ብለው ለመመንተፍ የተዘጋጁ፣ ለዚህ እንቅልፍ አጥተው የሚተጉ ወገኖች መኖራቸውን ነው። ከእነዚህ መሃከል አብዛኞቹ የፌደራል መንግስቱ ሥልጣን ከተቀማ ሃገሪቱ ዳግም አንድነቷን መመለስ በማይቻልበት ሁኔታ ትበታተናለች በሚል እምነት ኢትዮጵያን ለመበታተን በጥፍሩም በጥርሱም የሚተጋው የኤርትራው ሻአቢያ አደራጅቶ በገንዘብ እየደገፈ ያሰማራቸው ቡድኖች ናቸው። ግነቦት 7፣ ኦነግና ኦብነግን ለዚህ ማሳያነት መጥቀስ ይቻላል። 
እንግዲህ የተከበሩ አቶ ግርማ የህዝብን ሥልጣን ለመጠበቅ የሚተጋውን መንግስት ወቅሰው፣ የህዝብን ሥልጣን ከውክልና ውጭ ለመመንተፍ በጥፍሩም በጥርሱም የሚተጋውን አበጀ ብለው አሞግሰዋል፤ “ከፋቱ ምኑ ላይ ነው?” ብለው። የተከበሩ አቶ ግርማ ይህን ሲሉ ግንቦት 7፣ ኦነግ፣ ኦበነግና ሌሎች ሻአቢያ ኢትዮጵያን እንዲያተራምሱ የቀፈቀፋቸውን አስርና ሃያ አባላት ያላቸው የሽብር ቡድኖችን እየደገፉ መሆኑን ልብ በሉ። 
የተከበሩ አቶ ግርማ በዚህ አኳሃን በሻአቢያ ተላላኪነት ኢትዮጵያን ለማፈራረሰ የተደራጁትን ጨመሮ የህዝብን ሥልጣን ለመመንተፍ ለሚንቀሳቀሱት ቡድኖች አጋርነታቸውን ከገለፁ በኋላ፣ “የኢህአዴግ አይነት መንግስት ከደርግ እንዴት እንደሚሻል ማሰብ እያቃተኘ ነው።” ብለዋል። የተከበሩ አቶ ግርማ “ወታደራዊው ደርግና በወቅቱ በኢህአዴግ የሚመራው የኢፌዴሪ መንግሥት ተመሳሳይ ናቸው” እያሉን ነው። ልዩነታቸውን አያወቁም ማለት ነው። እናም ልዩነታቸውን መመልከት ይችሉ ዘንድ በአጭሩ ላስታውሳቸው።
3 
ኢህአዴግ ሥልጣን የያዘው በህዝብ ውክልና ነው። ወታደራዊው ደርግና ኢሠፓ ግን የህዝብ ውክልና አለነበራቸውም። አቶ ግርማ ይህን ለማገናዘብ የማይችሉ በእድሜ ለጋ ልጅ ናቸው የሚል ግምት የለኝም። በደርግ የሥልጣን ዘመን የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና አሁን በጎልማሳነት እደሜ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው። 
በኢፌዴሪ መንግስት ከወታደራዊው ደርግ በተቃራኒ ዜጎች የፈቀዱትን አመለካከት የመያዝ ሕገመንግስታዊ መብት አላቸው። መሰል አመለካከት ካላቸው ጋር የመደራጀት፣ በግልም በድርጅትም ለሥልጣን የመወዳደርና በህዝብ ውክልና ሥልጣን የመያዝም ሕገመንግስታዊ መብት አላቸው። እንግዲህ በዚህ ሕገመንግስታዊ መብት መሰረት ኢህአዴግ “የተለየ አቋም አለን” ከሚሉ ፓርቲዎች ጋር፣ ከአቶ ግርማ አንድነት ፓርቲ ጋር ጭምር ተፎካክሮ በምርጫ ሂደት ሕዝብ በሰጠው የሥልጣን ውክልና ወደ ሥልጣን የመጣ ፓርቲ ነው። ይህ ተጨባጭ እውነት ነው። 
የዚህን እውነትነት ከተከበሩ አቶ ግርማ በላይ የሚመሰክር ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም አቶ ግርማ በአዲስ አበባ ወረዳ 6 አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ወክለው ለፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተወዳድረው አብላጫ ድምፅ በማግኘት የአካባቢውን ሕዝብ የሥልጣን ውክልና ተረክበዋልና። 
በዚህ ምክንያት አቶ ግርማ ሕዝብ ሥልጣን በውክልና የሰጠበት ምርጫ ዴማክራሲያዊና ፍትሃዊ፣ ሕዝብ የተሳተፈበት፣ በአጠቃላይ ምርጫው ላይ አንዳችም ማጭበርበር ያልተፈፀመበ መሆኑን ልባቸወ ጠንቅቆ ያውቀዋል። የአቶ ግርማና የሌሎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አወካከል አንድና ተመሳሳይ ነው። ይህ በወታደራዊ ደርግ/ኢሠፓ የስልጣን ዘመን በፍፁም የማይታሰበ ነበር። አሁን ግን ተቸሏል። አቶ ግርማ ደግሞ ይህን በተግባር አይተውታል። 
በኢፌዴሪ መንግሥት የፈቀዱትን አመለካከት ከመያዝና ከማራመድ ጋር አመለካከትን/ሃሳብን የመግለፅ መብትም በሕገመንግስት ተረጋግጧል። ሃሳብን የመግለፅ መብት ተግባራዊ የሚሆንበትን የፕሬስ ነፃነትም ተረጋግጧል። አሁን ዜጎች የፈለጉትን የመናገር፤ በጋዜጣ፣ በመፅሄትና በመፀሃፍ የመፃፍ መብታቸውን አየተጠቀሙ ነው። አቶ
4 
ግርማ ይህን መብት በገፍ ከተጠቀሙት አንዱ ናቸው። ፓርላማ ውስጥ ያመኑበትን ሃሳብ ይናገራሉ፤ ደጋፊዎቻቸውን ሰብስበው አደባባይ ላይ የመሰላቸውን ያወራሉ፤ በሬድዮ ያወራሉ፤ በመፅሄትና ጋዜጦች ይፅፋሉ፤ በይፋ መንግስትን የሚተች መፅሃፍ አሳትመው አሰራጭተዋል። እንግዲህ፤ የተከበሩ አቶ ግርማ በኢፌዴሪ መንግስት የፈቀዱትን አመለካከት መያዝ ችለዋል፣ በአመለካከታቸው ተደራጀተዋል፤ አመለካከታቸውን በይፋ አራምደዋል፤ ለስልጣን ተፎካክረዋል፤ ውክልና አግኝተዋል፤ ሃሳባቸውን ያለምንም ክልከላ በተለያየ መንገድ ገልፀዋል። 
በወታደራዊው ደርግ/ኢሠፓ የሥልጣን ዘመን ይህን ማድረግ የማይታሰብ ነበር። ሥርአቱ ከሚከተለው አመለካከት ውጭ ይዞ መገኘት ያሳስራል፣ ያስገርፋል፣ ያስገድላል። ሃሳብን በይፋ መግለፅ ብቻ ሳይሆን ሌሎች በንግግር፣ በብሮድካስት፣ በፅሁፍ የገለፁትን ያዳመጠና ያነበበ ጭምር ከእሥር፣ ግርፋትና ሞት አይተርፍም ነበር። በወታደራዊው ደርግ የሥልጣን ዘመን በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በዘፈቀደ የተጨፈጨፉት የተለየ ወንጀል ሥለፈፀሙ አልነበረም። አቶ ግርማ አሁን በይፋ የሚያደርጉትን፣ የፈቀዱትን አመለካከት ለመያዝ፣ ለማራመድ፣ ለመግለፅ በመጠየቃቸውና ይህን ተግባራዊ ለማድረግ በመሞከራቸው ብቻ ነው። እናም የኢፌዴሪ የመንግሥት ሥርአት ፍፁም ከወታደራዊ ደርግ የተለየ ነው። 
አቶ ግርማ ይህን መብቶችና ነፃነቶች የተከበሩበትን እና የህዝብ ውክልና ያለው አካል ሥልጣን የተረከበበትን ሕገመንግሥታዊ የኢፌዴሪ የመንግስት ሥርአት ነው በጠመንጃ መጣል ተገቢ መሆኑን የነገሩን። አቶ ግርማ በወታደራዊወ ደርግና በኢፌዴሪ መንግስት መሃከል ያለውን እጅግ በጣም ሰፊ ልዩነት ማየት ለምን እንዳቃታቸው በፍፁም ሊገባኝ አይችልም። 
አቶ ግርማ መንግስትን በጠመንጃ ማስወገድ ተገቢ መሆኑን በገለፁበት ፅሁፍ፣ በቅረቡ አታሚዎቻቸው ከተከሰሱባቸው መፅሄቶችና ጋዜጦች ጋር በተያያዘ የሕትመታቸውን መቋረጥ የተመለከተ ጉዳይ አንሰተዋል። ይህም “. . . መንግሥት በየማተሚያ ቤቱ እየሄደ መፅሄትና ጋዜጣ ታትሙና ወየውላችሁ ማለቱን ተያይዞታል። ይህ ከሕግ ሥርአት ውጭ
5 
በየማተሚያ ቤቱ በግንባርና በሥልክ የሚደረገው ማስፈራሪያ ከወሮበላነት ውጭ ምንም ሊሆን አይችልም።” በሚል የገለፁት ነው። 
የተከበሩ አቶ ግርማ የማይመጥናቸውን “ወሮበላ” የሚለውን ያልተከበረ ፀያፍ ቃል ተጠቀመው መሳደብ እስኪችሉ ሃሳባቸውን የመግለፅ ነፃነታቸውን ያስከበረላቸው መንግሥት ማተሚያ ቤቶች መፅሄትና ጋዜጦችን እንዳያትሙ አልከለከለም። አሁንም በርካታ መፅሄቶችና ጋዜጦች ከመንግስት ማተሚያ ቤቶች ውጭ በግል ማተሚያ ቤቶች እየታተሙ ይሰራጫሉ። በመሆኑም በደፈናው “መንግሥት የግል ማተሚያ ቤቶች መፅሄቶችን እንዳያትሙ ከለከለ” የሚለው የተከበሩ አቶ ግርማ ያቀረቡት ውንጀላ ውሸትና መሰረተ ቢሥ ነው። በመገናኛ ብዙሃን እወነትነት የሌለው ወሬ ማውራት ደግሞ “ወሮበላ” ባያስብልም፣ “ውሸታም” ማስባሉ አይቀርም። 
እርግጥ ነው የግል ማተሚያ ቤቶች የተወሰኑ መፅሄቶችንና ጋዜጦችን አናትምም ብለው ሊሆን ይችላል። ይህን ያደረጉት ግን በመንግሥት ትእዛዝ አይደለም። እንዳያትሙ ያደረጋቸው ከዚህ ይልቅ የ1997 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጅል ሕግ ላይ የሰፈረ ድንጋጌ ነው፡፡ በወንጀል ሕጉ ምዕራፍ አራት ላይ “በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት በሚደረጉ ወንጀሎች ተካፋይ መሆን” በሚለው ርዕስ በአንቀፅ 42 የሚከተለው ተደንገጓል፡፡ በዚሁ አንቀፅ ነኡስ አንቀፅ 2 ላይ “በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት የሚደረጉ ወንጀሎች፤ በጋዜጦች፣ በመጻሕፍት፣ በበራሪ ጽሁፎች፣ በመጽሄቶች፣ በሚለጠፉ ወረቀቶች፣ ምስዕሎች፣ በሲኒማ፣ በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዢን ስርጭት ወይም በማናቸውም ሌላ የህዝብ መገናኛ በሆነ ዘዴ የሚደረጉ ናቸው” ይላል፡፡ 
ንኡስ አንቀጽ 3 ደግሞ “ወንጀሉ የተደረገው በነዚሁ በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት ከሆነ የሰውን ክብር በመንካት ብቻ ሳይሆን የግልን ወይም የጋራ ደህንነትን በመድፈርና በወንጀል ሕግ ተከብሮ የሚኖረውን ማናቸውንም ሕጋዊ መብት ምንካት ይጨምራል፤ ወንጀሉ ተፈጸመ የሚባለውም በነዚሁ ዘዴዎች በተገለጸ ግዜ ነው ” ይላል፡፡ 
ይሄው የወንጀል ሕግ፣ ወንጀሉ ተፈፅሞ ሲገኝ በሃላፊነት የሚጠየቁትንም በአንቀፅ 43 ላይ ይዘረዝራል፡፡ የተነሳንበት ጉዳይ የሚያተኩረው በየግዜው የሚወጡ የሕትምት ውጤቶች
6 
(መፅሄቶችና ጋዜጦች) በመሆናቸው ይህንኑ በሚመለከት ነኡስ አንቀፅ 1 ላይ ከ ሀ እስክ ሰ የፊደል ተራ የተዘረዘሩትን ጠቅለል አድርጌ እጠቅሳለሁ፡፡ ሕጉ በመጀመሪያ ተጠያቂነት የሚያስቀምጠው የፕሬስ ውጤቱ ሲታተም በዋና አዘጋጅነት ወይም በምክትል ዋና ዘዘጋጅነት የተመዘገበውን ግለሰብ ነው፡፡ 
ሕትመቱ በወጣበት ግዜ ፕሬሱ ፍቃድ የሌለው ከሆነ፣ ውይም ዋና አዘጋጅ የሆኑት ሰዎች ዋና አዘጋጅ ለመሆን የሚያበቁ ሁኔታዎችን የማያሟሉ ሆኖ ከተገኘ፣ ወይም በዋና አዘጋጅነት መስራታቸውን ያቆሙ ከሆነ የፕሬሱ አሳታሚ ኃላፊ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ የፕሬስ ውጤቱ በተሰራጨበት ወቅት፣ የፕሬሱን አሳታሚ ለማወቅ ካልተቻለ በኣሳታሚው ምትክ አታሚው ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 
በዚህ መሰረት አንድ የፕሬስ ውጤት ሕገወጥ የሆኑ ፅሁፎችን አትሞ ሲገኝ፣ ልክ የጋዜጣ /የመፅሔቱ ዋና አዘጋጆች ተጠያቂ እንደሚሆኑት፣ አታሚውም ተጠያቂ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡ እናም አታሚው ተገዶ ፍርድ ቤት እንዳይሄደ በህግ ሊያስጠይቅ የሚችል ይዘት ያለውንና አዘጋጆቹና አሳታሚዎቹ ላይገኙ የሚችሉ መፅሄትን ወይም ጋዜጣን ከማተም ይታቀባል። 
እንግዲህ ሰሞኑን አሳታሚዎቻቸው የተከሰሱት መፅሄቶችና ጋዜጦች አሳታሚዎቻቸው እንዲሁም አዘጋጆቻቸው ከሃገር እየኮበለሉ መሆኑ እየተነገረ በመሆኑ አታሚዎቹ (ማተሚያ ቤቶቹ) በሕግ ለመጠየቅ እየተጋለጡ ነው። በመሆኑም ማንም ሳያዛቸው ወይም ሳያስፈራራቸው ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ በሕግ የመጠየቅ መዘዝ ሊያመጡ የሚችሉ መፅሄቶችንና ጋዜጦችን አናትምም ማለታቸው አይቀሬ ነው። ይህን ማድረጋቸውም አስተዋይነት ነው፤ ዘግይተው ቢሆንም። እናም የተከበሩ አቶ ግርማ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ ሳይኖራቸው፣ ምንም አሳማኝ መከራከሪያ ሳያቀርቡ “መንግስት፣ የግል ማተሚያ ቤቶች መፅሄቶችንና ጋዜጦችን እንዳያትሙ ከለከለ።” በሚል ያቀረቡት ውንጀላ የተሳሳተ ነው። 
በአጠቃላይ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ “በጥፈሩም በጥርሱም ለሥልጣን የሚተጋ መንግስት እንዴት እንታገለው?” በሚል ርዕስ ያቀረቡት ፅሁፍ በኃይል ሥልጣን
7 
ለመመንተፍ ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖቸ አጋርነት የተገለፀበት፣ መሰረተ ቢስ ትችቶች የቀረቡበትና ከአንድ ይሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የማይጠበቅ የዘቀጠ ነው።

Mais conteúdo relacionado

Semelhante a Coment on-ato-girma- seyfu speeches, on x eth pm meles

Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi) founder, Professo...
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professo...Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professo...
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi) founder, Professo...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Zethiopia Newspaper Jan 2014
Zethiopia Newspaper Jan 2014Zethiopia Newspaper Jan 2014
Zethiopia Newspaper Jan 2014derejedesta
 
ስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdf
ስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdfስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdf
ስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdfmarakiwmame
 
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs
Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs  Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Semelhante a Coment on-ato-girma- seyfu speeches, on x eth pm meles (6)

Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi) founder, Professo...
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professo...Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professo...
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi) founder, Professo...
 
Zethiopia Newspaper Jan 2014
Zethiopia Newspaper Jan 2014Zethiopia Newspaper Jan 2014
Zethiopia Newspaper Jan 2014
 
ስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdf
ስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdfስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdf
ስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdf
 
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs
Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs  Ethiopian federal Democratic Unity (  Medrek) major-policies &  programs
Ethiopian federal Democratic Unity ( Medrek) major-policies & programs
 
Ende hagher eninegagher/...let us discuss as a country
Ende hagher eninegagher/...let us discuss as a countryEnde hagher eninegagher/...let us discuss as a country
Ende hagher eninegagher/...let us discuss as a country
 
Safeguarding Training amharic.ppt
Safeguarding Training amharic.pptSafeguarding Training amharic.ppt
Safeguarding Training amharic.ppt
 
Mais de Ethio-Afric News en Views Media!!

VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capitalAddis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capitalEthio-Afric News en Views Media!!
 
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the... conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Mais de Ethio-Afric News en Views Media!! (20)

The impact of_the_ethiopian oromo_protests 2016
The impact of_the_ethiopian oromo_protests 2016The impact of_the_ethiopian oromo_protests 2016
The impact of_the_ethiopian oromo_protests 2016
 
History of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
History of Ethiopian General Jagema kealo , in AmharicHistory of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
History of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
 
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
 
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capitalAddis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capital
 
Ethiopia eritrea contradictions 2015
Ethiopia eritrea contradictions 2015Ethiopia eritrea contradictions 2015
Ethiopia eritrea contradictions 2015
 
Thanks/ Misgana
Thanks/ MisganaThanks/ Misgana
Thanks/ Misgana
 
Joint statement on_the_election
Joint statement on_the_electionJoint statement on_the_election
Joint statement on_the_election
 
The ark of the covenant
The ark of the covenant The ark of the covenant
The ark of the covenant
 
Arkofthecovenent
ArkofthecovenentArkofthecovenent
Arkofthecovenent
 
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
 
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the... conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
 
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
 
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
 
Moto menesat sene1999
Moto menesat sene1999Moto menesat sene1999
Moto menesat sene1999
 
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
 
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
 
King of kings yohannes & ethiopian unity 5
King of kings yohannes & ethiopian unity 5King of kings yohannes & ethiopian unity 5
King of kings yohannes & ethiopian unity 5
 
King of kings yohannes & ethiopian unity 4
King of kings yohannes & ethiopian unity 4King of kings yohannes & ethiopian unity 4
King of kings yohannes & ethiopian unity 4
 
King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3
King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3
King of Kings Yohannes & Ethiopian unity 3
 
Coment on-ato-girma- seyfu speeches, on x eth pm meles

  • 1. 1 ሥልጣን በኃይል ለመቀማት ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች የተገለፀ አጋርነት ለሚ ዋቄ 09-08-14 የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በቅርቡ ውጭ ሃገር በሚገኙ ደረ ገፆች አንድ ፅሁፍ አስነብበውናል። “በጥፈሩም በጥርሱም ለሥልጣን የሚተጋ መንግስት እንዴት እንታገለው?” በሚል ርዕሥ የቀረበውን ፅሁፍ መጀመሪያ ስመለከተው የኢፌዴሪ መንግስት ከፍተኛው የሥልጣን አካል የሆነው የህዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት አባል የማይጠበቅ በመሆኑ እርግጥ የተከበሩ አቶ ግርማ ሠይፉ የፃፉት መሆኑን ተጠራጥሬያለሁ። እርግጥ አሁንም አቶ ግርማ በጤናቸው ሆነው የፃፉት ነው የሚል እመነት የለኝም። ፅሁፉን አቶ ግርማ ፅፈውትም ይሁን ሌላ ሰው በስማቸው ፅፎት ይዘቱን ስለማይቀይረው የፅሁፉ ይዘት ላይ ላተኩር። በአጠቃላይ ፅሁፉ ከሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ባህርይ ያፈነገጠና ሕገወጥነት ቀመስ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ፃፉት የተባለው ፅሁፍ “. . . መንግስትን በሁሉም አቀፍ ትግል መጣል አለብን ብለው ጠብ መንጃ ቢያነሱ ክፋቱ ምን ላይ እንደሆነ አልታይህ እያለኝ ነው።” በሎ ነው የሚጀምረው። ይህን አቋም እንዲይዙ ያደረጋቸው ደግሞ መንግስት “በጥፍሩም በጥርሱም ለሥልጣን የሚተጋ” በመሆኑ እንደሆነ ነግረውናል። የተከበሩ አቶ ግርማ ከላይ የተጠቀሰውን ሃሳብ ሲያሰፍሩ አንድ የዘነጉት ወይም ሆን ብለው የዘለሉት ነገር መኖሩ ይሰማኛል። ይህም ገዢው ፓርቲ ወደ ሥልጣን የመጣው በቸኛ የመንግሥት ሥልጣን ምንጭና ባለቤት በሆነው ሕዝብ የሥልጣን ውክልና ተሰጥቶት መሆኑን ነው። ታዲያ ገዢው ፓርቲ የመንግሥትን ኃላፊነት ሲረከብ ይህን የህዝብ ሥልጣን ከህዝብ ውክልና ውጭ ሥልጣን ለመያዝ ከሚንቀሳቀሱ ቡድኖች በጥፍሩም በጥርሱም ለመጠበቅ መትጋት ይጠበቅበታል። ይህን ማደረጉ ከማንኛውም መንግሥት የሚጠበቅና ተገቢ ነው። መንግስት ሕዝብ በውክልና የሰጠውን ሥልጣን፣ ማንኛውም ሥልጣን ናፋቂ ቡድን መንትፎ መውሰድ
  • 2. 2 እነዲችል እንቅልፋም መሆን የለበትም። ይህን የሚያደርግ ከሆነ መንግስተ የመሆን ብቃት የለውም ማለት ነው። ሥልጣን ከህዝብ በአደራ የሚሰጥ በመሆኑ ከማንኛውም ቀማኛ በጥፍርም በጥርስም መጠበቅ አለበት። ችግር የሚሆነው በጥፍርና በጥርስ መጠበቅ የማይችል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የተከበሩ አቶ ግርማ ሊያስታውሱት የሚገባው ሌላው ጉዳይ የመንግስትን ሥልጣን በጥፍርም በጥርስም ብለው ለመመንተፍ የተዘጋጁ፣ ለዚህ እንቅልፍ አጥተው የሚተጉ ወገኖች መኖራቸውን ነው። ከእነዚህ መሃከል አብዛኞቹ የፌደራል መንግስቱ ሥልጣን ከተቀማ ሃገሪቱ ዳግም አንድነቷን መመለስ በማይቻልበት ሁኔታ ትበታተናለች በሚል እምነት ኢትዮጵያን ለመበታተን በጥፍሩም በጥርሱም የሚተጋው የኤርትራው ሻአቢያ አደራጅቶ በገንዘብ እየደገፈ ያሰማራቸው ቡድኖች ናቸው። ግነቦት 7፣ ኦነግና ኦብነግን ለዚህ ማሳያነት መጥቀስ ይቻላል። እንግዲህ የተከበሩ አቶ ግርማ የህዝብን ሥልጣን ለመጠበቅ የሚተጋውን መንግስት ወቅሰው፣ የህዝብን ሥልጣን ከውክልና ውጭ ለመመንተፍ በጥፍሩም በጥርሱም የሚተጋውን አበጀ ብለው አሞግሰዋል፤ “ከፋቱ ምኑ ላይ ነው?” ብለው። የተከበሩ አቶ ግርማ ይህን ሲሉ ግንቦት 7፣ ኦነግ፣ ኦበነግና ሌሎች ሻአቢያ ኢትዮጵያን እንዲያተራምሱ የቀፈቀፋቸውን አስርና ሃያ አባላት ያላቸው የሽብር ቡድኖችን እየደገፉ መሆኑን ልብ በሉ። የተከበሩ አቶ ግርማ በዚህ አኳሃን በሻአቢያ ተላላኪነት ኢትዮጵያን ለማፈራረሰ የተደራጁትን ጨመሮ የህዝብን ሥልጣን ለመመንተፍ ለሚንቀሳቀሱት ቡድኖች አጋርነታቸውን ከገለፁ በኋላ፣ “የኢህአዴግ አይነት መንግስት ከደርግ እንዴት እንደሚሻል ማሰብ እያቃተኘ ነው።” ብለዋል። የተከበሩ አቶ ግርማ “ወታደራዊው ደርግና በወቅቱ በኢህአዴግ የሚመራው የኢፌዴሪ መንግሥት ተመሳሳይ ናቸው” እያሉን ነው። ልዩነታቸውን አያወቁም ማለት ነው። እናም ልዩነታቸውን መመልከት ይችሉ ዘንድ በአጭሩ ላስታውሳቸው።
  • 3. 3 ኢህአዴግ ሥልጣን የያዘው በህዝብ ውክልና ነው። ወታደራዊው ደርግና ኢሠፓ ግን የህዝብ ውክልና አለነበራቸውም። አቶ ግርማ ይህን ለማገናዘብ የማይችሉ በእድሜ ለጋ ልጅ ናቸው የሚል ግምት የለኝም። በደርግ የሥልጣን ዘመን የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና አሁን በጎልማሳነት እደሜ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው። በኢፌዴሪ መንግስት ከወታደራዊው ደርግ በተቃራኒ ዜጎች የፈቀዱትን አመለካከት የመያዝ ሕገመንግስታዊ መብት አላቸው። መሰል አመለካከት ካላቸው ጋር የመደራጀት፣ በግልም በድርጅትም ለሥልጣን የመወዳደርና በህዝብ ውክልና ሥልጣን የመያዝም ሕገመንግስታዊ መብት አላቸው። እንግዲህ በዚህ ሕገመንግስታዊ መብት መሰረት ኢህአዴግ “የተለየ አቋም አለን” ከሚሉ ፓርቲዎች ጋር፣ ከአቶ ግርማ አንድነት ፓርቲ ጋር ጭምር ተፎካክሮ በምርጫ ሂደት ሕዝብ በሰጠው የሥልጣን ውክልና ወደ ሥልጣን የመጣ ፓርቲ ነው። ይህ ተጨባጭ እውነት ነው። የዚህን እውነትነት ከተከበሩ አቶ ግርማ በላይ የሚመሰክር ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም አቶ ግርማ በአዲስ አበባ ወረዳ 6 አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ወክለው ለፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተወዳድረው አብላጫ ድምፅ በማግኘት የአካባቢውን ሕዝብ የሥልጣን ውክልና ተረክበዋልና። በዚህ ምክንያት አቶ ግርማ ሕዝብ ሥልጣን በውክልና የሰጠበት ምርጫ ዴማክራሲያዊና ፍትሃዊ፣ ሕዝብ የተሳተፈበት፣ በአጠቃላይ ምርጫው ላይ አንዳችም ማጭበርበር ያልተፈፀመበ መሆኑን ልባቸወ ጠንቅቆ ያውቀዋል። የአቶ ግርማና የሌሎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አወካከል አንድና ተመሳሳይ ነው። ይህ በወታደራዊ ደርግ/ኢሠፓ የስልጣን ዘመን በፍፁም የማይታሰበ ነበር። አሁን ግን ተቸሏል። አቶ ግርማ ደግሞ ይህን በተግባር አይተውታል። በኢፌዴሪ መንግሥት የፈቀዱትን አመለካከት ከመያዝና ከማራመድ ጋር አመለካከትን/ሃሳብን የመግለፅ መብትም በሕገመንግስት ተረጋግጧል። ሃሳብን የመግለፅ መብት ተግባራዊ የሚሆንበትን የፕሬስ ነፃነትም ተረጋግጧል። አሁን ዜጎች የፈለጉትን የመናገር፤ በጋዜጣ፣ በመፅሄትና በመፀሃፍ የመፃፍ መብታቸውን አየተጠቀሙ ነው። አቶ
  • 4. 4 ግርማ ይህን መብት በገፍ ከተጠቀሙት አንዱ ናቸው። ፓርላማ ውስጥ ያመኑበትን ሃሳብ ይናገራሉ፤ ደጋፊዎቻቸውን ሰብስበው አደባባይ ላይ የመሰላቸውን ያወራሉ፤ በሬድዮ ያወራሉ፤ በመፅሄትና ጋዜጦች ይፅፋሉ፤ በይፋ መንግስትን የሚተች መፅሃፍ አሳትመው አሰራጭተዋል። እንግዲህ፤ የተከበሩ አቶ ግርማ በኢፌዴሪ መንግስት የፈቀዱትን አመለካከት መያዝ ችለዋል፣ በአመለካከታቸው ተደራጀተዋል፤ አመለካከታቸውን በይፋ አራምደዋል፤ ለስልጣን ተፎካክረዋል፤ ውክልና አግኝተዋል፤ ሃሳባቸውን ያለምንም ክልከላ በተለያየ መንገድ ገልፀዋል። በወታደራዊው ደርግ/ኢሠፓ የሥልጣን ዘመን ይህን ማድረግ የማይታሰብ ነበር። ሥርአቱ ከሚከተለው አመለካከት ውጭ ይዞ መገኘት ያሳስራል፣ ያስገርፋል፣ ያስገድላል። ሃሳብን በይፋ መግለፅ ብቻ ሳይሆን ሌሎች በንግግር፣ በብሮድካስት፣ በፅሁፍ የገለፁትን ያዳመጠና ያነበበ ጭምር ከእሥር፣ ግርፋትና ሞት አይተርፍም ነበር። በወታደራዊው ደርግ የሥልጣን ዘመን በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በዘፈቀደ የተጨፈጨፉት የተለየ ወንጀል ሥለፈፀሙ አልነበረም። አቶ ግርማ አሁን በይፋ የሚያደርጉትን፣ የፈቀዱትን አመለካከት ለመያዝ፣ ለማራመድ፣ ለመግለፅ በመጠየቃቸውና ይህን ተግባራዊ ለማድረግ በመሞከራቸው ብቻ ነው። እናም የኢፌዴሪ የመንግሥት ሥርአት ፍፁም ከወታደራዊ ደርግ የተለየ ነው። አቶ ግርማ ይህን መብቶችና ነፃነቶች የተከበሩበትን እና የህዝብ ውክልና ያለው አካል ሥልጣን የተረከበበትን ሕገመንግሥታዊ የኢፌዴሪ የመንግስት ሥርአት ነው በጠመንጃ መጣል ተገቢ መሆኑን የነገሩን። አቶ ግርማ በወታደራዊወ ደርግና በኢፌዴሪ መንግስት መሃከል ያለውን እጅግ በጣም ሰፊ ልዩነት ማየት ለምን እንዳቃታቸው በፍፁም ሊገባኝ አይችልም። አቶ ግርማ መንግስትን በጠመንጃ ማስወገድ ተገቢ መሆኑን በገለፁበት ፅሁፍ፣ በቅረቡ አታሚዎቻቸው ከተከሰሱባቸው መፅሄቶችና ጋዜጦች ጋር በተያያዘ የሕትመታቸውን መቋረጥ የተመለከተ ጉዳይ አንሰተዋል። ይህም “. . . መንግሥት በየማተሚያ ቤቱ እየሄደ መፅሄትና ጋዜጣ ታትሙና ወየውላችሁ ማለቱን ተያይዞታል። ይህ ከሕግ ሥርአት ውጭ
  • 5. 5 በየማተሚያ ቤቱ በግንባርና በሥልክ የሚደረገው ማስፈራሪያ ከወሮበላነት ውጭ ምንም ሊሆን አይችልም።” በሚል የገለፁት ነው። የተከበሩ አቶ ግርማ የማይመጥናቸውን “ወሮበላ” የሚለውን ያልተከበረ ፀያፍ ቃል ተጠቀመው መሳደብ እስኪችሉ ሃሳባቸውን የመግለፅ ነፃነታቸውን ያስከበረላቸው መንግሥት ማተሚያ ቤቶች መፅሄትና ጋዜጦችን እንዳያትሙ አልከለከለም። አሁንም በርካታ መፅሄቶችና ጋዜጦች ከመንግስት ማተሚያ ቤቶች ውጭ በግል ማተሚያ ቤቶች እየታተሙ ይሰራጫሉ። በመሆኑም በደፈናው “መንግሥት የግል ማተሚያ ቤቶች መፅሄቶችን እንዳያትሙ ከለከለ” የሚለው የተከበሩ አቶ ግርማ ያቀረቡት ውንጀላ ውሸትና መሰረተ ቢሥ ነው። በመገናኛ ብዙሃን እወነትነት የሌለው ወሬ ማውራት ደግሞ “ወሮበላ” ባያስብልም፣ “ውሸታም” ማስባሉ አይቀርም። እርግጥ ነው የግል ማተሚያ ቤቶች የተወሰኑ መፅሄቶችንና ጋዜጦችን አናትምም ብለው ሊሆን ይችላል። ይህን ያደረጉት ግን በመንግሥት ትእዛዝ አይደለም። እንዳያትሙ ያደረጋቸው ከዚህ ይልቅ የ1997 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጅል ሕግ ላይ የሰፈረ ድንጋጌ ነው፡፡ በወንጀል ሕጉ ምዕራፍ አራት ላይ “በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት በሚደረጉ ወንጀሎች ተካፋይ መሆን” በሚለው ርዕስ በአንቀፅ 42 የሚከተለው ተደንገጓል፡፡ በዚሁ አንቀፅ ነኡስ አንቀፅ 2 ላይ “በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት የሚደረጉ ወንጀሎች፤ በጋዜጦች፣ በመጻሕፍት፣ በበራሪ ጽሁፎች፣ በመጽሄቶች፣ በሚለጠፉ ወረቀቶች፣ ምስዕሎች፣ በሲኒማ፣ በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዢን ስርጭት ወይም በማናቸውም ሌላ የህዝብ መገናኛ በሆነ ዘዴ የሚደረጉ ናቸው” ይላል፡፡ ንኡስ አንቀጽ 3 ደግሞ “ወንጀሉ የተደረገው በነዚሁ በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት ከሆነ የሰውን ክብር በመንካት ብቻ ሳይሆን የግልን ወይም የጋራ ደህንነትን በመድፈርና በወንጀል ሕግ ተከብሮ የሚኖረውን ማናቸውንም ሕጋዊ መብት ምንካት ይጨምራል፤ ወንጀሉ ተፈጸመ የሚባለውም በነዚሁ ዘዴዎች በተገለጸ ግዜ ነው ” ይላል፡፡ ይሄው የወንጀል ሕግ፣ ወንጀሉ ተፈፅሞ ሲገኝ በሃላፊነት የሚጠየቁትንም በአንቀፅ 43 ላይ ይዘረዝራል፡፡ የተነሳንበት ጉዳይ የሚያተኩረው በየግዜው የሚወጡ የሕትምት ውጤቶች
  • 6. 6 (መፅሄቶችና ጋዜጦች) በመሆናቸው ይህንኑ በሚመለከት ነኡስ አንቀፅ 1 ላይ ከ ሀ እስክ ሰ የፊደል ተራ የተዘረዘሩትን ጠቅለል አድርጌ እጠቅሳለሁ፡፡ ሕጉ በመጀመሪያ ተጠያቂነት የሚያስቀምጠው የፕሬስ ውጤቱ ሲታተም በዋና አዘጋጅነት ወይም በምክትል ዋና ዘዘጋጅነት የተመዘገበውን ግለሰብ ነው፡፡ ሕትመቱ በወጣበት ግዜ ፕሬሱ ፍቃድ የሌለው ከሆነ፣ ውይም ዋና አዘጋጅ የሆኑት ሰዎች ዋና አዘጋጅ ለመሆን የሚያበቁ ሁኔታዎችን የማያሟሉ ሆኖ ከተገኘ፣ ወይም በዋና አዘጋጅነት መስራታቸውን ያቆሙ ከሆነ የፕሬሱ አሳታሚ ኃላፊ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ የፕሬስ ውጤቱ በተሰራጨበት ወቅት፣ የፕሬሱን አሳታሚ ለማወቅ ካልተቻለ በኣሳታሚው ምትክ አታሚው ተጠያቂ ይሆናል፡፡ በዚህ መሰረት አንድ የፕሬስ ውጤት ሕገወጥ የሆኑ ፅሁፎችን አትሞ ሲገኝ፣ ልክ የጋዜጣ /የመፅሔቱ ዋና አዘጋጆች ተጠያቂ እንደሚሆኑት፣ አታሚውም ተጠያቂ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡ እናም አታሚው ተገዶ ፍርድ ቤት እንዳይሄደ በህግ ሊያስጠይቅ የሚችል ይዘት ያለውንና አዘጋጆቹና አሳታሚዎቹ ላይገኙ የሚችሉ መፅሄትን ወይም ጋዜጣን ከማተም ይታቀባል። እንግዲህ ሰሞኑን አሳታሚዎቻቸው የተከሰሱት መፅሄቶችና ጋዜጦች አሳታሚዎቻቸው እንዲሁም አዘጋጆቻቸው ከሃገር እየኮበለሉ መሆኑ እየተነገረ በመሆኑ አታሚዎቹ (ማተሚያ ቤቶቹ) በሕግ ለመጠየቅ እየተጋለጡ ነው። በመሆኑም ማንም ሳያዛቸው ወይም ሳያስፈራራቸው ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ በሕግ የመጠየቅ መዘዝ ሊያመጡ የሚችሉ መፅሄቶችንና ጋዜጦችን አናትምም ማለታቸው አይቀሬ ነው። ይህን ማድረጋቸውም አስተዋይነት ነው፤ ዘግይተው ቢሆንም። እናም የተከበሩ አቶ ግርማ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ ሳይኖራቸው፣ ምንም አሳማኝ መከራከሪያ ሳያቀርቡ “መንግስት፣ የግል ማተሚያ ቤቶች መፅሄቶችንና ጋዜጦችን እንዳያትሙ ከለከለ።” በሚል ያቀረቡት ውንጀላ የተሳሳተ ነው። በአጠቃላይ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ “በጥፈሩም በጥርሱም ለሥልጣን የሚተጋ መንግስት እንዴት እንታገለው?” በሚል ርዕስ ያቀረቡት ፅሁፍ በኃይል ሥልጣን
  • 7. 7 ለመመንተፍ ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖቸ አጋርነት የተገለፀበት፣ መሰረተ ቢስ ትችቶች የቀረቡበትና ከአንድ ይሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የማይጠበቅ የዘቀጠ ነው።