O slideshow foi denunciado.
Seu SlideShare está sendo baixado. ×

Ethiopia Tamrt Ppt.pptx

Anúncio
Anúncio
Anúncio
Anúncio
Anúncio
Anúncio
Anúncio
Anúncio
Anúncio
Anúncio
Anúncio
Anúncio
Carregando em…3
×

Confira estes a seguir

1 de 18 Anúncio

Mais Conteúdo rRelacionado

Anúncio

Ethiopia Tamrt Ppt.pptx

 1. 1. የደ/ማርቆስ ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኢትዮጵያ ታምርት የንቅናቄ መድረክ
 2. 2. 1. መግቢያ ታሪካዊቷና ጥንታዊቷ ከተማ ደብረማርቆስ የበርካታ ፀጋዎች ባለቤት ብትሆንም ያላትን ሀብትና የመልማት ዕድል በአግባቡ ሳትጠቀምበት በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ከተማችን ምንም እንኳን የበርካታ ፀጋዎች ባለቤት ብንሆንም ፀጋዎችን አውጥቶ ለመጠቀም የሚስችል ምቹ ሁኔታ ባለመፈጠሩ ምክንያት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴሰሰችን እጅግ ደካማ ሆኖ ቆይተል፡፡ በከተማችን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ጅማሮው ከ2003 ዓ.ም ወዲህ ቢሆንም በነበሩ ስርዓት ወለድ የተንዛዛ ቢሮክራሲ እና አስተዳደራዊ በደሎች የተነሳ ባለሀብቶች ተስፋ በመቁረጥ ከተማችንን ከማልማት ይልቅ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሲያማትሩ ቆይተዋል፡፡ ይሁንም እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለዘረርፉ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረትየከተማችን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መነቃቃት እየታየበት ይገኛል፡፡
 3. 3. በከተማችን ልዩልዩ ኢንዱስትሪዎች በተለያዩ ዘርፎች ቦታ ተረክበው በእንቅስቃሴ ላይ ሲሆኑ ከእነዚህ እንዱስትሪዎች መካከል 24ቱ ግንባታቸውን አጠናቀው ወደ ምርት ስራ የገቡ ናቸው፡፡ አራት ኢንዱስትሪዎች ደግሞ በማሽን ተከላ ላይ ሲሆኑ በቅርቡ ወደ ማምረት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አሁን አሁን በራሳቸው ተነሳሽነትም ይሁን በተሰሩ የፕሮሞሽን ስራዎች ወደ ከተማችን ኢንቨስት ለማድረግ የሚመጡ ባለሀብቶች ቁጥር እየተበራከተ መጥተል፡፡ ይህንን የባለሀብት ፍሰት በአግባቡ ጥያቄውን መመለስ ከተቻለ ደብረ ማርቆስ ከተማን የተሸለ ተመራጭና ተወዳዳሪ ማድረግ ይቻላል፡፡
 4. 4. ይህንን ታሳቢ በማድረግ መምሪያችን በአዲስ መደራጀቱን ተከትሎ በአዲስ ስሜት ፕሮጀክቶችን ወደ አፈጻጸም ከማስገባት እና መሰረተ ልማት እንዲሟላና የኢንዱስትሪ ሽግግር ለማምጣት ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት ከመስራት አንጻር የነበረው እንቅስቃሴ አበረታች ነበር፡፡ ዘርፉ ለከተማቸን ዕድገት የሚጫወተውን ቁልፍ ሚና በመገንዘብና በክልሉ የተነደፉ ግቦችን ለማሳካት የ2015 እቅድን ሰፋ አድርጎ በማቀድ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ከተማችን በቅርቡ ወደ ሪጅኦ ፖሊታን ከተማ ማደጓን ተከትሎ በደ/ማርቆስ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ የወረዳ ቀበሌዎች ከአነደድ ወረዳ የወቢ እነችፎ 34.84 ስኩዌር ኪ/ሜ ስፋት፣ ወንጋ ንፋሳም 43.64 ስኩዌር ኪ/ሜ ስፋት በአጠቃላይ 78.48 ስኩዌር ኪ/ሜ ስፋት እንዲሁም ከጎዛምን ወረዳ የቦ አርጀና 24.98 ስኩዌር ኪ/ሜ ስፋት፣ ወንቃ 42.22 ስኩዌር ኪ/ሜ ስፋት፣
 5. 5. • እነራታ 35.12 ስኩዌር ኪ/ሜ ስፋት፣ ቀቢ 59.45 ስኩዌር ኪ/ሜ ስፋት በአጠቃላይ 161.75 ስኩዌር ኪ/ሜ ስፋት የተካለለ ሲሆን የደ/ማርቆስ ከተማ 52.35 ስኩዌር ኪ/ሜ ስፋት የነበራት ሲሆን አሁን 292.57 ስኩዌር ኪ/ሜ ሲሆን አሁን ላይ በርካታ ባለሀብቶች አዲስ ፕሮጀክት ቀርፀው ወደ ከተማችን እየመጡ በመሆኑ የኢንቨስትመንት ቦታ ጥያቄ ለሚያቀርቡት የተሻለ አገልግሎት እንድናቀርብ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ • ስለሆነም የከተማችንን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በሚፈለገው ሁኔታ ለመምራትና በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍተታተ በየጊዜው ከአጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ ዛሬ በከተማችን እየተካሄደ ለሚገኘው የ ‘‘ኢትዮጵያ ታምርት’’ የንቅናቄ መድረክ ላይ ለምክክር ይሆን ዘንድ ይህ የውይይት የመነሻ ፅሁፍ ተዘጋጅተል፡፡
 6. 6. የመድረኩ ዓላማ ፡- • የከተማችንን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በንቅናቄ ለመምራት፤ በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመፍታት፤ በኢንዱስትሪዎች መካከል የእርስበእርስ የልምድ ክውውጥ እንዲኖር ዕድል መፍጠር እንዲሁም በከተማችን በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ለጠየቁ ባለሃብቶች መሬት በምናስተላልፍበት ወቅት ላይ በመሆናችን በቂ መግባባት ላይ ለመድረስ እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ነው፡፡
 7. 7. ስለ ደብረማርቆስ ከተማ ኢንቨስትመንት በጥቂቱ • ለግዙፍና ቀላል ኢንዱስትሪዎች ተመራጭ እየሆነች የመጣችው ደብረ ማርቆስ ከተማ በአፍሪካ ደረጃ ተጠቃሸ ከሆኑ ኢንዱስትሪዎች የቅባት እህሎች፣ የዘይት ፋብሪካ፣ የዱቄት ፋብሪካ፣ የግብርና ውጤቶችና ሌሎች የኢንዱስተሪ ምርቶች ማዕከል እየሆነች የመጣች ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የሚበረታቱ የተለያዩ ተቋማት ግንባታ ማለትም የጤና እና የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች የከተማዋ የወደፊት ውበቶች እና የመልማት አቅሟን የሚጎለብቱ እምቅ ፀጋዎች ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
 8. 8. በከተማችን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የተጀመረው በ 2003 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ፡  በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከ110 በላይ ኢንዱስትሪዎች በተለያዩ ዘርፎች ቦታ ተረክበው በእንቅስቃሴ ላይ ሲሆኑ ከእነዚህ እንዱስትሪዎች መካከል  24ቱ ግንባታቸውን አጠናቀው ወደ ምርት ስራ የገቡ  4ቱ ኢንዱስትሪዎች ግንባታቸውን አጠናቀው ማሽን ተከላ ላይ ያሉ  16ቱ ግንባታቸውን አጠናቀው ማሽን ለማስገባት በዝግጅት ላይ ያሉ  46ቱ በግንባታ ላይ የሚገኙ  20ዎቹ ደግሞ በቅድመ ግንባታ ላይ የሚገኙ ናቸው ፡፡
 9. 9. በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መሬት የወሰዱ ባለሃብቶች በዓ.ም ሲታይ 2 1 0 15 5 24 8 23 14 8 10 0 5 10 15 20 25 30 35 2003 ዓ.ም 2004 ዓ.ም 2005 ዓ.ም 2006 ዓ.ም 2007 ዓ.ም 2008 ዓ.ም 2009 ዓ.ም 2010 ዓ.ም 2011 ዓ.ም 2012 ዓ.ም 2013 ዓ.ም 2014 ዓ.ም የባለሀብቱ ብዛት
 10. 10. በተገቢው ሁኔታ ወደ ስራ ባለመግባታቸው የወሰዱትን መሬት የተነጠቁ ፕሮጀክቶች
 11. 11. የአዳዲስ ፕሮጀክቶችን መሬት ጥያቄ ለመመለስ የተከናወኑ ተግባራት • ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን ደብረ ማርቆስ ኢንቨስት ለማድረግ ጥያቄ እያቀረበ ያለው ባለሀብት ቁጥር እየተበራከተ በመምጣቱ ምክንያት በከተማችን ተጨማሪ የኢንዱስትሪ ቦታዎችን በሳይት ፕላን ማካለል በማስፈለጉ ፡- ከ1200 ሄክታር በላይ መሬት በላይ እንዲካለል ተደርገል ከዚህ ውስጥ ደግሞ 140 ሄክታር መሬት የካሳ ስሌቱ ተጠናቅቆ ለባለሀብቶቹ ለማስተላለፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ይህንን መሬት በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ ከአርሶ አደሮች እና ሌሎች አጋር አካላት ጋር ከመመካከር ጀምሮ በርካታ ውጣ ውረዶች ታልፈዋል፡፡
 12. 12. የመሬት ማስተላለፍ ስራችን የዘገየበት ምክንያት ከዚህ በፊት የተላለፉ የኢንቨስትመንት ቦታዎች በአግባቡ ወደ ተግባር አለመቀየራቸው፤ ከአርሶ አደሮች ጋር ለመተማመን የወሰደው ጊዜ የአርሶ አደሩ መሬት በተለያዩ ደላሎች በተለያዬ አግባብ ግብይት በመፈጸም አሁንም ዘርፉ ላይ እንቅፋት እየሆኑ በመሆኑ (ክስ) የካሳ ስሌቱ በሚፈለገው ፍጥነት ያለመጠናቀቅ በባለ ድርሻ አካላት መካከል የነበረ መገፋፋት
 13. 13. ከመሬት ዝግጅት አንፃር የተከናወኑ ተግባራት  በከተማችን በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመሰማራት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ፕሮጀክታቸው ተገምግመው አልፈው መሬት በመጠባበቅ ላይ የሚገኙት 113 ባለሃብቶች 240.5ሄ/ር መሬት ካሳ ከፍለው ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡  ችግሮቻችንን ጎን ለጎን እየፈታን የተከለለው 140 ሄ/ር መሬት ግን የካሳ ስሌቱ እንዲጠናቀቅ የተቋቋመው ኮሚቴ ስራውን እያስኬደ ነው፤
 14. 14. ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ሁለገብ ኢንዱስትሪ መንደሩ ለባለሃብቶች ተላልፎ ያለቀ በመሆኑ ተጨማሪ በሳይት ፕላን አስደግፎ አስረክቦናል፤ ከህጋዊ የመሬት ባለ ይዞታዎች ጋር በርካታ መድረኮችን በመፍጠር የኢንቨስትመንት ልማቱ እንዲቀጥል በቂ መግባባት መፍጠር ችለናል፡፡
 15. 15. ያጋጠሙ ችግሮች የአርሶ አደሮች የእርስ በርስ የመሬት ይገባኛል ክርክሮች፤ አርሶ አደሩ ለልጆቹ የቤት መስሪያ ቦታ ጥያቄ የተገቢነት ሁኔታ፤ ጥያቄዎች እስከ ፍርድ ቤት ድረስ የዘለቁ መሆናቸው፤ የአርሶ አደሩን ጥያቄዎች ለመፍታት የተሄደበት ርቀት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ድርሻቸውን ይወጡ ዘንድ ተከታታይ መድረኮችን በመፍጠር ጥያቄዎችን እንደተገቢነታቸው ለመመለስ ጥረት ተደርጉዋል፡፡
 16. 16. አሁን የደረስንበት አፈፃፀም ለኢንቨስትመንት የሚውሉ መሬቶችን ለማልማት ይቻል ዘንድ ከአርሶ አደሮች ጋር በቂ መግባባት ላይ ደርሰናል፤  የካሳ ግምት ስራን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ለመፈጸም የሚያስችል ስምሪት ተሰጥቶ ስራውን ማጠናቀቅ ተችሏል፤ የኢንቨስትመንት ቦታ የሚተላለፍላቸውን ባለሃብቶች የልየታ ስራ ተከናውኗል፤
 17. 17. ከባለሃብቱ ምን ይጠበቃል? የካሳ ክፍያ ገንዘብ በወቅቱ ገቢ ማድረግ፤ መሬት የሚተላለፍላቸው አልሚ ባለሃብቶች በውላቸው መሰረት ፈጥኖ ወደ ስራ መግባት፤

×