SlideShare uma empresa Scribd logo
1 de 11
Baixar para ler offline
በስመ Aብ ወወልድበስመ Aብ ወወልድ
ወመንፈስቅዱስ Aሐዱ Aምላክ
Aሜን፡፡Aሜን፡፡
Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብOርቶዶክሳዊ - ቤተሰብ
ክፍል አምስት
መምህር፡‐ ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ
E‐mail: kesisolomon4@gmail.com
ቦታ፡‐ ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ
በየሳምንቱ ረቡዕ ምሽት ከ12፡30 – 1፡30
ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም.
Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
ርEሰ ጉዳያችንን Aስመልክቶ ቅዱስ ጳውሎስ በክርስቶስ Iየሱስ Aብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና• ርEሰ ጉዳያችንን Aስመልክቶ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በክርስቶስ Iየሱስ Aብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና
ለAቂላ ሰላምታ Aቅርቡልኝ፤ Eነርሱም ስለ ነፍሴ ነፍሳቸውን ለሞት Aቀረቡ፥ የAሕዛብም Aብያተ
ክርስቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኑAቸው ናቸው Eንጂ Eኔ ብቻ Aይደለሁም፤ በቤታቸውም ላለች
ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ Aቅርቡልኝ። ከEስያ ለክርስቶስ በኵራት ለሆነው ለምወደው ለAጤኔጦን
ሰላምታ Aቅርቡልኝ።›› ሮሜ 16፡3-5፡፡ Eንዲሁም ‹‹በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን
በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ Aቅርቡልን።›› ቆላ 4፡15፡፡ በማለት የጻፈው በመጽሐፍበቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ Aቅርቡልን።›› ቆላ 4፡15፡፡ በማለት የጻፈው በመጽሐፍ
ቅዱሳችን ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
• ስለዚህ ‹‹በቤታቸው ያለች ቤተ ክርስቲያን›› ማለት ምን ማለት ነው?
• በዘመነ ሐዋርያት የነበረችው ቤተ ክርስቲያን በክርስትና Eምነት ባመኑ Aማንያን ቤት ሆና
በIየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ለጸሎት የሚሰበሰቡባት ነበረች፡፡
• የመጀመሪያይቱም ቤተ ክርስቲያን የማርቆስ Eናት የማርያም ቤት ነበረች፡፡ ‹‹ባስተዋለም ጊዜ• የመጀመሪያይቱም ቤተ ክርስቲያን የማርቆስ Eናት የማርያም ቤት ነበረች፡፡ ‹‹ባስተዋለም ጊዜ
Eጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ Eናት ወደ
ማርያም ቤት መጣ።›› የሐዋ 12፡12፡፡
• Eንዲሁም ያመኑት በጵርስቅላና በAቂላ Eንዲሁም በንምፉን Eና በልድያ ቤት ይሰበሰቡ Eንደነበር
Eናነባለን፡፡ የሐዋ 16፤ 18 Eና ቆላ 4፡15፡፡
Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
ት• Eነዚህን ጥቅሶች በዚህ መልክ ወስደን ካልተረጎምናቸው ጥቅሶቹን Eንዴት በሕይወታችን
ልንጠቀምባቸው Eንችላለን?
• ወደ ቤቱ ስንገባ በውስጡ የሚገኙት፣ የሚያገለግሉትና የሚገለገሉበት Eነማን Eንደሆኑ በግድግዳው
ላይ በሰቀሉAቸው ሥEላት ለመለየት የሚያስችል Eድል Eናገኛለን፡፡
• ስፖርትን ወይም ሙዚቃን የሚያዘወትሩ ሰዎች በቤታቸው ግድግዳ በሰቀሉት ፎቶ ፍላጎታቸው ምን
Eንደሆነ Aድናቆታቸውም ለማን Eንደሆነ ለመለየት Eንደምንችለው ሁሉ OርቶዶክሳውያንEንደሆነ Aድናቆታቸውም ለማን Eንደሆነ ለመለየት Eንደምንችለው ሁሉ Oርቶዶክሳውያን
ክርስቲያኖችም በቤታቸው ሃይማኖታቸው ምን Eንደሆነ ያሳውቃሉ ወይም ያስረዳሉ፡፡
• Eንደ ክርስቲያን በቤታችን የተሰቀሉት ምን ዓይነት ሥEላትና ፎቶግራፎች ናቸው? በቤታችንስ ቤተ
ት ኛ ችክርስቲያን ትገኛለች?
• የIትዮጵያ Oርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥEላት ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ያላቸውን
ጠቀሜታ በመገንዘብ ለቤት ማድመቂያነት ከማዋል ይልቅ ከፍተኛ ክብካቤ Eንዲደረግላቸው ታላቅ
ጥንቃቄ ታደርግላቸዋለች፡፡
• በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ሥEላት ሰማያዊቱ ቤተ ክርስቲያን በምድር ከEኛ ጋር ያላትን Aንድነት ያመለክታሉ፡፡
በሰማያዊቱ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ የEግዚAብሔር ቅዱሳን በሥEላቸው ተወክለው በምድር ባለችው ቤተ
ክርስቲያን ይገኛሉና፡፡ የቅዱሳኑን፣ የመላEክቱን ሥEል ስንመለከት ነፍሳችን በተመስጦ ሆና ከበጎነታቸው
ትማራለች፣ በጸሎታቸውና በAማላጅነታቸውም Eንዲረዱን ትጠይቃለች፡፡
Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
• ሥEላት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ነጸብራቅ ናቸው፡፡ ቅዱሳን ሥEላት የተማሩትም ያልተማሩትም በፊደል
ቋንቋ ሳይሆን በቀላማት Aስረጅነት መንፈሳዊውን ዓለምና ሕይወት ለመረዳት Eንዲችሉ ያደርጋሉ፡፡
• ሥEላት በጥንቃቄ ከተሳሉ ታሪክን ወክለው ይገኛሉ፡፡ ይልቁኑ የIትዮጵያ Oርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን ሥEላት መንፋሳዊውንና ታሪካዊውን ገጽታ ቁልጭ Aድርገው በቀላሉ የማሳየት ጉልበት Aላቸው፡፡
• በቤታችን የሚገኙ ቅዱሳን ሥEላት በቤተሰቡ Aባላትና በሥEላቱ በተገለጹት ቅዱሳን መካከል
የተፈጠረውን Aንድነት ከየትኛውም Aስረጅ ነገር በላይ ማሳየት የሚችሉ ገላጮች ናቸው፡፡
• በቅዱሳን ሥEላት የተከበበች ቤተ ክርስቲያን በቤታችን Aለችን? Eነዚህ ሥEላትስ ክርስትናችንንበቅዱሳን ሥEላት የተከበበች ቤተ ክርስቲያን በቤታችን Aለችን? Eነዚህ ሥEላትስ ክርስትናችንን
ብሎም Oርቶዶክሳዊነታችንን መግለጽ ይቻላቸዋል?
• ለምሳሌ በመለኮታዊ ኃይሉ ሲገለጥ ማንም ሊያየው የማይቻለው የEግዚAብሔር Aብ፣ የEግዚAብሔር
ቅ ች ኛ ትወልድ፣ የEግዚAብሔር መንፈስ ቅዱስ ሥEል በቤታችን ይገኛል? ምስጢረ ቁርባን የተመሠረተበትና
የተፈጸመበት የምሴተ ሐሙስ ሥEልስ? ማቴ 17፣ ማቴ 3፣ ማቴ 26፡፡
• በመዝ 44፡9፡፡ ‹‹በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።›› በማለት
Eንደተጻፈልን Eመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታችን በቀኝ በኩል ሆና Eንደታቀፈችው
የምትታይበት ሥEልስ በቤታችን Aለን? በቤታችን በምንሰቅላቸው ሥEላት ላይ ታላቅ ጥንቃቄ ማድረግ
ይገባናል፡፡ይገባናል
• የተወደዳችሁ የEግዚAብሔር ቤተሰቦች! Aሁን የትኞቹ ሥEላት Eንደሚገኙ ለመመልከት ወደ
Oርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ቤት በመግባት ቅኝት Eናደርጋለን፡፡
Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
• ወደ Oርቶዶክሳውያን ቤት ስንገባ ክፉ ሁሉ ወደ ቤቱ Eንዳይቀርብ፣ ቤቱም ቤተ ክርስቲያን ሆና• ወደ Oርቶዶክሳውያን ቤት ስንገባ ክፉ ሁሉ ወደ ቤቱ Eንዳይቀርብ፣ ቤቱም ቤተ ክርስቲያን ሆና
የጌታችን ፈቃዱ Eንዲፈጸምባትና ደስ Eንዲሰኝባት በመግቢያው ላይ የሊቀ መላEክት ቅዱስ ሚካኤል
ሥEል የቤቱ ጠባቂ ይሆን ዘንድ ተሰቅሎ ልንመለከት Eንችላለን፡፡ መዝ 33፡7-8፡፣ማቴ 18፡10፡፡
• የመላEክት Aለቃ ቅዱስ ሚካኤል ጌታችን Aምላካችን Iየሱስ ክርስቶስ የሚገባባትንና ከAመኑበት
Oርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ጋር የሚኖርባትን ቤት የመግቢያ በር ይጠብቃታል፡፡
በቤቱ መግቢያ ላይ
• ‹‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።›› ማቴ 11፡28፡፡ በማለት Eንደሚጣራ ሆኖ
Eጆቹን ዘርግቶ የተሰቀለውን የጌታችን Aምላካችን Iየሱስ ክርስቶስን ሥEል ልናገኝ Eንችላላን፡፡
• ይህም ሥEል ወደዚህ ቤት የሚገቡትን ሁሉ ችግር፣ ሸክምና ፈተና በራሱ በማኖር ሰላምን ይሰጣቸው• ይህም ሥEል ወደዚህ ቤት የሚገቡትን ሁሉ ችግር፣ ሸክምና ፈተና በራሱ በማኖር ሰላምን ይሰጣቸው
ዘንድ ይጋብዛቸዋል፡፡ ገላ 3፡1፡፡
• በተጨማሪም በዚሁ ቤት መግቢያ ላይ በስደቱ የግብጽና የIትዮጵያን ሰዎች የባረከበትን የስደቱን
ሥEል ልናገኝ Eንችላለን፡፡
• ይህን ሥEል በቤታችን መግቢያ ላይ ማድረጋችን ጌታችን ከEመቤታችንና ከቅዱስ ዮሴፍ ጋር
Eንዲባርከን ያደርገናል፡፡ Iሳ 19፡25፣ Eንባ 3፡7፡፡
• Eንግዲህ ይህን በማድረግ የጌታችን የAምላካችንን በረከት ከEናቱ ከEመቤታችንና ከቅዱሳኑ ጋር
ወደምንቀበልበትና ሰላም ወደሞላበት ቤታችን Eንግባ፡፡
Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
በማረፊያ ክፍል (Living Room)
• ጌታችን በተራራው ስብከት ሲያስተምር የሚያመለክተውን ሥEል ልናደርግ Eንችላላን፡፡ ማቴ 5 - 8፡፡
• ይህንም ሥEል ስንመለከት የጌታችንን ቃሉን Eያስታወስን (Eያሰብን) ሰውነታችንንም Eየተቆታጠርን
ሕይወታችንንም የቃሉ ምስክርነት የሚሰጥበት ልናደርገው Eንችላለን፡፡
ይህን ቦታ ቤተሰቡ ሁሉ ከEንግዶቻቸው ጋር የሚሰባሰቡበትና ስለ Aምላካችን ትEዛዛት የሚነጋገሩበት• ይህን ቦታ ቤተሰቡ ሁሉ ከEንግዶቻቸው ጋር የሚሰባሰቡበትና ስለ Aምላካችን ትEዛዛት የሚነጋገሩበት
ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
በማEድ ቤት
• ጌታችን Aምላካችን በAምስት Eንጀራና በሁለት ዓሣ Aምስት ሺህ ሕዝብ መግቦ ያትረፈረፈበት ሥEል
ሊኖር ይችላል፡፡ ማቴ 14፡14-22፡፡
• ይህን ሥEል ስንመለከት ያለን ሀብትና የክፍፍሉ Aለመመጣጠን ወይም ማነስ የማይገድበውን ሁሉን
Aትረፍርፎ የሚሰጠውን የጌታችንን በረከቱን (ስጦታውን) Eናስተውላለን፡፡
• ወላጆች ጌታችን ሕዝቡን ከመመገቡ በፊት ስለዘላለማዊቱ መንግሥት ስለመንግስተ ሰማያት
በማስተማር ከሥጋ ፍላጎታቸው በፊት መንፈሳዊውን ያሚላ መሆኑን ልብ ማለት ይገባቸዋል፡፡በማስተማር ከሥጋ ፍላጎታቸው በፊት መንፈሳዊውን ያሚላ መሆኑን ልብ ማለት ይገባቸዋል፡፡
• በዚህም መሠረት ለልጆቼ መንፈሳዊ ፍላጎታቸውን Eያሚላሁላቸው ነው ወይስ ሐሳብ ብቻ
የማመላልስ ነኝ? ብሎ ራስን መጠየቅም ያስፈልጋል፡፡
• ወላጆች ከቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች Eያነበብን ያነበብነውንም ትርጉም ተምረን በመረዳት ለልጆቻችን
Eንደ ሥጋዊ ምግባቸው መንፈሳዊ ምግባቸውን Eናዘጋጅላቸዋለን?
Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
• በማEድ ቤታችን ከዚሁ በተጨማሪ የማርታና የማርያም ሥEል ሊኖረን ይችላል፡፡ ሉቃስ 10፡38-42፡፡
Eል ስ ለከት ታች ታ ት ሽ ት ሽ• ይህን ሥEል ስንመለከት ጌታችን ማርታን ‹‹ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው
ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።፡፡›› ሉቃ 10፡41-42፡፡
በማለት የነገራትን ቃሉን Eናስታውሳለን፡፡
• ወላጆችም ይህን Aቅጣጫ በመከተል ማንኛውንም ነገር ከማድረጋቸው በፊት ማርያም Eንዳደረገችው
ከጌታችን Eግር ሥር በመቀመጥ ከEግዚAብሔር ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ማጥበቅና በጥልቅ መሠረት
ላይ ማነጽ ይገባቸዋል፡፡ላይ ማነጽ ይገባቸዋል፡፡
• ወላጆች በዚህ ዘመን ማርያምንም ማርታንም ሆነው መገኘታቸው Eጅግ Aስፈላጊ ነው፡፡
በመመገቢያ ክፍላችን (Dinning Room)
• Oርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የመመገቢያ ክፍላችንን በፍራፍሬዎችና በAበቦች ከማድመቅ ይልቅ
‹‹የሚበላኝ ደግሞ ከEኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።›› ዮሐ 6፡57፡፡ ያለውንና የሕይወት Eንጀራ የሆነውን
ጌታችን Aምላካችንን የምናስብበት የምሴተ ሐሙስ ሥEል ብናደርግ መልካም ነው፡፡
• ይህን ሥEል ስንመለከት ከቅዱስ ቁርባን መራቃችንን ልናስታውስ Eንችላለን፡፡
• በተጨማሪም በሥEሉ የሚገኘውን ይሁዳን ስንመለከት ኃጢAታችን ከቅዱስ ቁርባን ምን ያህል
Eንዳራቀንና ከቅዱሳንም Aንድነት Eንደለየን Eናስተውላለን፡፡Eንዳራቀንና ከቅዱሳንም Aንድነት Eንደለየን Eናስተውላለን፡፡
• Eየተመገብን ሥEሉን መመልከታችን ልባችንም መንፈሳዊውን ምግብ Eንዲመገብ ምክንያት ይሆነዋል
Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
የባለትዳሮች የመኝታ ክፍል
• በቃና ዘገሊላ ተገኝቶ ጋብቻን የባረከ የጌታችን ሥEል ሊኖር ይችላል፡፡ ዮሐ 2፡1-11፡፡
• የሥEሉ መኖር ጌታችን ከEናቱ ከEመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር
በሠርግ ቤቱ ተገኝቶ ጋብቻውን Eንደባረከ በዚህም ቤት በመካከላቸው ተገኝቶ ሐሳባቸውን
Eንደባረከላቸውና በፍቅርም Eንዳስተሳሰራቸው Eንዲሰማቸው፣ Eንዲረዱ Eንዲያስተውሉ ይረዳል፡፡Eንደባረከላቸውና በፍቅርም Eንዳስተሳሰራቸው Eንዲሰማቸው፣ Eንዲረዱ Eንዲያስተውሉ ይረዳል፡፡
በልጆቻችን ክፍል
• በልጆች ክፍል ውስጥ ብዙ ጊዜ ሚኪ ማውስን (Mickey Mouse) የመሳሰሉ የEንስሳትና የAEዋፋት
ሥEሎች (ፎቶዎች) Eናገኛለን፡፡
• የOርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ቤት ግን ከልጆቹ Aልጋ በላይ የሚጠብቋቸው መላEክት ሥEል
በሌላኛው በኩል በሚገኘው ግድግዳ ላይ ደግሞ ሕጻናትን የሚወዳቸውና ያቀፋቸው በሕጻናት
የተከበበው የጌታችን ሥEል ይኖራል፡፡ ማቴ 19፡13-15፣ ማቴ 18፡1-10፡፡
• በተጨማሪም በከብቶች ግርግም የተወለደው የጌታችንንና በሕጻንነቱ ሰማEት የሆነው የቅዱስ ቂርቆስ
ሥEላት በልጆች ክፍል ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ማቴ 2፣ Eብ 12፡1 3፡፡ሥEላት በልጆች ክፍል ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ማቴ 2፣ Eብ 12፡1-3፡፡
• ይህም ጎዳናቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ለጌታችን ለAምላካችንና ለቅዱሳኑም ቅርቦች ሆነው
መንፈሳዊውን ዓለም በAግባቡ Eየተረዱና መንፈሳዊነቱም Eየተዋሃዳቸው Eንዲያድጉ ይረዳቸዋል፡፡
• የተወደዳችሁ ምEመናን! የOርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ቤት በቅዱሳን ሥEላት ብቻ ሳይሆን በተለያየ
ቅርጽ በተሠሩ መስቀሎችም ጭምር የተባረከ ነው፡፡ ገላ 6፡14፣ ፊል 3፡18-21፡፡
Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን
• ተፈጥሮን የሚያደንቁና የሚወዱም በመዝ 91(92)፡12 ‹‹ጻድቅ Eንደ ዘንባባ ያፈራል፥ Eንደ ሊባኖስ ዝግባም
ል E ለ ሳ ጎ ለ ት Aቸ ዘ Eላት ሊያድጋል።›› Eንደተባለው ወደ መንፈሳዊ ጎዳና ለማምራት የሚረዱAቸውን የዘንባባ… ሥEላት ሊያደርጉ
ይችላሉ፡፡
• ዘንባባ ግንዱ ቢታይም ሥሩ ግን Aይታይም፡፡ ለግንዱ ሕይወቱ ሥሩ ነው፡፡ በዚሁ ዛፍ ሥEል Aማካኝነት
የማይታየው EግዚAብሔር የሚታየውን ሰው ከፍጥረታት ሁሉ Aልቆ ሲመግበውና ሲያበረታው የሚኖር
መሆኑን Eንማርበታለን፡፡
• የዘንባባ ዛፍ ግንድ ውስጣዊ Aካሉ ነጭ መሆኑ ‹‹ ክፉውን በመልካም Aሸንፍ Eንጂ በክፉ Aትሸነፍ።›› ሮሜ
12፡21፡፡ የተባለውንና በዚህም Eየተመራ የሚኖረውን የጻድቁን ሰው የልብ ንጽሕና ያመለክተናል፡፡
• የዘንባባ ዛፍ ድንጋይ ሲወረውሩበት ወይም ሲያወዛውዙት ፍሬውን Eንደሚያራግፍ ሁሉ ጻድቅ ሰውም ቅዱስ
Eስጢፋኖስ ‹‹ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢAት Aትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።›› የሐዋ 7፡60፡፡ በማለት
Eንዳደረገው ቅዱሳን በጭቃኔና በግፍ ለሚፈታተኑAቸው ሁሉ የሚጸልዩላቸው መሆኑን Eንማርበታለን፡፡
• በመዝ 18(19)፡1፡፡ ‹‹ሰማያት የEግዚAብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የEጁን ሥራ ያወራል።››
በማለት መዝሙረኛው ዳዊት Eንደዘመረው የEግዚAብሔርን ድንቅ ሥራ ለማሰብ ይረዳን ዘንድዊ ዚ ይ
የከዋክብትና የጨረቃም ሥEላት በቤታችን ሊኖሩ ይችላሉ፡፡
• የEግዚAብሔር ቤተሰቦች! የሰው ወገኖች በጎበኟችሁ ጊዜ ሁሉ በቤታችሁ የምትገኘውን ቤተ ክርስቲያን
ሊያገኟት ሊመለከቷት ይችሉ ይሆን? ቤተሰቡ ሁሉ የሚጠቀምባቸውን መንፈሳውያን ሥEላትስ ይመለከቱሊያገኟት ሊመለከቷት ይችሉ ይሆን? ቤተሰቡ ሁሉ የሚጠቀምባቸውን መንፈሳውያን ሥEላትስ ይመለከቱ
ይሆን? … ይቆየን፡፡
ይቆየን፡፡ይቆየን
For your queries or questions E‐mail: 
kesisolomon4@gmail.com
T t ll th l fTo get all the lessons, surf :
www.zeorthodox.org

Mais conteúdo relacionado

Mais procurados (11)

Volume 1
Volume 1Volume 1
Volume 1
 
Orthodox yoth life skill 2
Orthodox yoth life skill 2Orthodox yoth life skill 2
Orthodox yoth life skill 2
 
Orthodox tewahedomarriage5wb
Orthodox tewahedomarriage5wbOrthodox tewahedomarriage5wb
Orthodox tewahedomarriage5wb
 
Orthodox christianfamilylesson11
Orthodox christianfamilylesson11Orthodox christianfamilylesson11
Orthodox christianfamilylesson11
 
Benson commentary
Benson commentaryBenson commentary
Benson commentary
 
Come holy spirit (amaric ethiopia)
Come holy spirit (amaric ethiopia)Come holy spirit (amaric ethiopia)
Come holy spirit (amaric ethiopia)
 
ልደተ ክርስቶስ
    ልደተ ክርስቶስ    ልደተ ክርስቶስ
ልደተ ክርስቶስ
 
ልደተ ክርስቶስ
ልደተ ክርስቶስልደተ ክርስቶስ
ልደተ ክርስቶስ
 
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw finalBibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
 
Abews proverb
Abews proverbAbews proverb
Abews proverb
 
Orthodox tewahedomarriage7wb
Orthodox tewahedomarriage7wbOrthodox tewahedomarriage7wb
Orthodox tewahedomarriage7wb
 

Destaque

Analisis kebijakan indonesia meratifikasi asean agreement on transboundary ha...
Analisis kebijakan indonesia meratifikasi asean agreement on transboundary ha...Analisis kebijakan indonesia meratifikasi asean agreement on transboundary ha...
Analisis kebijakan indonesia meratifikasi asean agreement on transboundary ha...Dwi Anggraini
 
Moringa Advantages
Moringa AdvantagesMoringa Advantages
Moringa Advantagesamberwill48
 
Cyber ID Sleuth Data Security Forensics
Cyber ID Sleuth Data Security ForensicsCyber ID Sleuth Data Security Forensics
Cyber ID Sleuth Data Security Forensicsbtr-security
 
Instructional design and development 7.06.14
Instructional design and development 7.06.14Instructional design and development 7.06.14
Instructional design and development 7.06.14jilllove1
 
More subjects
More subjectsMore subjects
More subjectsCHARMY22
 
Jaquet multitasker
Jaquet multitaskerJaquet multitasker
Jaquet multitaskerPaul Andrew
 

Destaque (12)

งานคอม
งานคอมงานคอม
งานคอม
 
Analisis kebijakan indonesia meratifikasi asean agreement on transboundary ha...
Analisis kebijakan indonesia meratifikasi asean agreement on transboundary ha...Analisis kebijakan indonesia meratifikasi asean agreement on transboundary ha...
Analisis kebijakan indonesia meratifikasi asean agreement on transboundary ha...
 
Industrial Replacement by Pruek
Industrial Replacement by PruekIndustrial Replacement by Pruek
Industrial Replacement by Pruek
 
Moringa Advantages
Moringa AdvantagesMoringa Advantages
Moringa Advantages
 
Cyber ID Sleuth Data Security Forensics
Cyber ID Sleuth Data Security ForensicsCyber ID Sleuth Data Security Forensics
Cyber ID Sleuth Data Security Forensics
 
02 e
02 e02 e
02 e
 
Tuntutan untuk orangtua
Tuntutan untuk orangtuaTuntutan untuk orangtua
Tuntutan untuk orangtua
 
Instructional design and development 7.06.14
Instructional design and development 7.06.14Instructional design and development 7.06.14
Instructional design and development 7.06.14
 
Contas con calc
Contas con calcContas con calc
Contas con calc
 
More subjects
More subjectsMore subjects
More subjects
 
สร้างบล็อก
สร้างบล็อกสร้างบล็อก
สร้างบล็อก
 
Jaquet multitasker
Jaquet multitaskerJaquet multitasker
Jaquet multitasker
 

Semelhante a Orthodox christianfamilylesson05

ሰባቱ የዕለት ጸሎት ጊዜያት (Seven Daily Prayer Times - Ethiopian Orthodox Tewahedo)
ሰባቱ የዕለት ጸሎት ጊዜያት (Seven Daily Prayer Times - Ethiopian Orthodox Tewahedo)ሰባቱ የዕለት ጸሎት ጊዜያት (Seven Daily Prayer Times - Ethiopian Orthodox Tewahedo)
ሰባቱ የዕለት ጸሎት ጊዜያት (Seven Daily Prayer Times - Ethiopian Orthodox Tewahedo)treson1
 
የቤተሰብ ህይወት ክፍል.pptx
የቤተሰብ ህይወት ክፍል.pptxየቤተሰብ ህይወት ክፍል.pptx
የቤተሰብ ህይወት ክፍል.pptxGetachewEndale
 
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptxየመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptxGetachewEndale
 
Abune bernabase
Abune bernabaseAbune bernabase
Abune bernabaseFikaduLemi
 
መሙቤቤት ህብረት.pptx
መሙቤቤት ህብረት.pptxመሙቤቤት ህብረት.pptx
መሙቤቤት ህብረት.pptxGetachewEndale
 
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptxKEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptxarmoniumtvkiw
 
ተግበራዊ ክርስትና.pdf
ተግበራዊ ክርስትና.pdfተግበራዊ ክርስትና.pdf
ተግበራዊ ክርስትና.pdfzelalem13
 
Bibl study power_point_aragaw_final[1]
Bibl study power_point_aragaw_final[1]Bibl study power_point_aragaw_final[1]
Bibl study power_point_aragaw_final[1]Henok Eshetie
 
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdfከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdfssuser0a3463
 
ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)
ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)
ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)YiftaleamZerizgi1
 

Semelhante a Orthodox christianfamilylesson05 (17)

ሰባቱ የዕለት ጸሎት ጊዜያት (Seven Daily Prayer Times - Ethiopian Orthodox Tewahedo)
ሰባቱ የዕለት ጸሎት ጊዜያት (Seven Daily Prayer Times - Ethiopian Orthodox Tewahedo)ሰባቱ የዕለት ጸሎት ጊዜያት (Seven Daily Prayer Times - Ethiopian Orthodox Tewahedo)
ሰባቱ የዕለት ጸሎት ጊዜያት (Seven Daily Prayer Times - Ethiopian Orthodox Tewahedo)
 
የቤተሰብ ህይወት ክፍል.pptx
የቤተሰብ ህይወት ክፍል.pptxየቤተሰብ ህይወት ክፍል.pptx
የቤተሰብ ህይወት ክፍል.pptx
 
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptxየመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
 
Orthodox tewahedomarriage6wb
Orthodox tewahedomarriage6wbOrthodox tewahedomarriage6wb
Orthodox tewahedomarriage6wb
 
Orthodox tewahedomarriage8wb
Orthodox tewahedomarriage8wbOrthodox tewahedomarriage8wb
Orthodox tewahedomarriage8wb
 
Abune bernabase
Abune bernabaseAbune bernabase
Abune bernabase
 
121
121121
121
 
መሙቤቤት ህብረት.pptx
መሙቤቤት ህብረት.pptxመሙቤቤት ህብረት.pptx
መሙቤቤት ህብረት.pptx
 
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptxKEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
 
Orthodox christianfamilylesson08
Orthodox christianfamilylesson08Orthodox christianfamilylesson08
Orthodox christianfamilylesson08
 
Orthodox christianfamilylesson02
Orthodox christianfamilylesson02Orthodox christianfamilylesson02
Orthodox christianfamilylesson02
 
ተግበራዊ ክርስትና.pdf
ተግበራዊ ክርስትና.pdfተግበራዊ ክርስትና.pdf
ተግበራዊ ክርስትና.pdf
 
Bibl study power_point_aragaw_final[1]
Bibl study power_point_aragaw_final[1]Bibl study power_point_aragaw_final[1]
Bibl study power_point_aragaw_final[1]
 
Tigrinya - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdf
Tigrinya - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdfTigrinya - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdf
Tigrinya - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdf
 
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdfከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
 
ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)
ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)
ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)ውዳሴ ማርያም ( ሰኑይ-ሰንበት)
 
Amharic - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdf
Amharic - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdfAmharic - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdf
Amharic - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdf
 

Orthodox christianfamilylesson05

  • 1. በስመ Aብ ወወልድበስመ Aብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ Aሐዱ Aምላክ Aሜን፡፡Aሜን፡፡
  • 2. Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብOርቶዶክሳዊ - ቤተሰብ ክፍል አምስት መምህር፡‐ ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ E‐mail: kesisolomon4@gmail.com ቦታ፡‐ ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ በየሳምንቱ ረቡዕ ምሽት ከ12፡30 – 1፡30 ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም.
  • 3. Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን ርEሰ ጉዳያችንን Aስመልክቶ ቅዱስ ጳውሎስ በክርስቶስ Iየሱስ Aብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና• ርEሰ ጉዳያችንን Aስመልክቶ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በክርስቶስ Iየሱስ Aብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለAቂላ ሰላምታ Aቅርቡልኝ፤ Eነርሱም ስለ ነፍሴ ነፍሳቸውን ለሞት Aቀረቡ፥ የAሕዛብም Aብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኑAቸው ናቸው Eንጂ Eኔ ብቻ Aይደለሁም፤ በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ Aቅርቡልኝ። ከEስያ ለክርስቶስ በኵራት ለሆነው ለምወደው ለAጤኔጦን ሰላምታ Aቅርቡልኝ።›› ሮሜ 16፡3-5፡፡ Eንዲሁም ‹‹በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ Aቅርቡልን።›› ቆላ 4፡15፡፡ በማለት የጻፈው በመጽሐፍበቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ Aቅርቡልን።›› ቆላ 4፡15፡፡ በማለት የጻፈው በመጽሐፍ ቅዱሳችን ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ • ስለዚህ ‹‹በቤታቸው ያለች ቤተ ክርስቲያን›› ማለት ምን ማለት ነው? • በዘመነ ሐዋርያት የነበረችው ቤተ ክርስቲያን በክርስትና Eምነት ባመኑ Aማንያን ቤት ሆና በIየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ለጸሎት የሚሰበሰቡባት ነበረች፡፡ • የመጀመሪያይቱም ቤተ ክርስቲያን የማርቆስ Eናት የማርያም ቤት ነበረች፡፡ ‹‹ባስተዋለም ጊዜ• የመጀመሪያይቱም ቤተ ክርስቲያን የማርቆስ Eናት የማርያም ቤት ነበረች፡፡ ‹‹ባስተዋለም ጊዜ Eጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ Eናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።›› የሐዋ 12፡12፡፡ • Eንዲሁም ያመኑት በጵርስቅላና በAቂላ Eንዲሁም በንምፉን Eና በልድያ ቤት ይሰበሰቡ Eንደነበር Eናነባለን፡፡ የሐዋ 16፤ 18 Eና ቆላ 4፡15፡፡
  • 4. Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን ት• Eነዚህን ጥቅሶች በዚህ መልክ ወስደን ካልተረጎምናቸው ጥቅሶቹን Eንዴት በሕይወታችን ልንጠቀምባቸው Eንችላለን? • ወደ ቤቱ ስንገባ በውስጡ የሚገኙት፣ የሚያገለግሉትና የሚገለገሉበት Eነማን Eንደሆኑ በግድግዳው ላይ በሰቀሉAቸው ሥEላት ለመለየት የሚያስችል Eድል Eናገኛለን፡፡ • ስፖርትን ወይም ሙዚቃን የሚያዘወትሩ ሰዎች በቤታቸው ግድግዳ በሰቀሉት ፎቶ ፍላጎታቸው ምን Eንደሆነ Aድናቆታቸውም ለማን Eንደሆነ ለመለየት Eንደምንችለው ሁሉ OርቶዶክሳውያንEንደሆነ Aድናቆታቸውም ለማን Eንደሆነ ለመለየት Eንደምንችለው ሁሉ Oርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችም በቤታቸው ሃይማኖታቸው ምን Eንደሆነ ያሳውቃሉ ወይም ያስረዳሉ፡፡ • Eንደ ክርስቲያን በቤታችን የተሰቀሉት ምን ዓይነት ሥEላትና ፎቶግራፎች ናቸው? በቤታችንስ ቤተ ት ኛ ችክርስቲያን ትገኛለች? • የIትዮጵያ Oርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥEላት ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ያላቸውን ጠቀሜታ በመገንዘብ ለቤት ማድመቂያነት ከማዋል ይልቅ ከፍተኛ ክብካቤ Eንዲደረግላቸው ታላቅ ጥንቃቄ ታደርግላቸዋለች፡፡ • በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ሥEላት ሰማያዊቱ ቤተ ክርስቲያን በምድር ከEኛ ጋር ያላትን Aንድነት ያመለክታሉ፡፡ በሰማያዊቱ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ የEግዚAብሔር ቅዱሳን በሥEላቸው ተወክለው በምድር ባለችው ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉና፡፡ የቅዱሳኑን፣ የመላEክቱን ሥEል ስንመለከት ነፍሳችን በተመስጦ ሆና ከበጎነታቸው ትማራለች፣ በጸሎታቸውና በAማላጅነታቸውም Eንዲረዱን ትጠይቃለች፡፡
  • 5. Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን • ሥEላት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ነጸብራቅ ናቸው፡፡ ቅዱሳን ሥEላት የተማሩትም ያልተማሩትም በፊደል ቋንቋ ሳይሆን በቀላማት Aስረጅነት መንፈሳዊውን ዓለምና ሕይወት ለመረዳት Eንዲችሉ ያደርጋሉ፡፡ • ሥEላት በጥንቃቄ ከተሳሉ ታሪክን ወክለው ይገኛሉ፡፡ ይልቁኑ የIትዮጵያ Oርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥEላት መንፋሳዊውንና ታሪካዊውን ገጽታ ቁልጭ Aድርገው በቀላሉ የማሳየት ጉልበት Aላቸው፡፡ • በቤታችን የሚገኙ ቅዱሳን ሥEላት በቤተሰቡ Aባላትና በሥEላቱ በተገለጹት ቅዱሳን መካከል የተፈጠረውን Aንድነት ከየትኛውም Aስረጅ ነገር በላይ ማሳየት የሚችሉ ገላጮች ናቸው፡፡ • በቅዱሳን ሥEላት የተከበበች ቤተ ክርስቲያን በቤታችን Aለችን? Eነዚህ ሥEላትስ ክርስትናችንንበቅዱሳን ሥEላት የተከበበች ቤተ ክርስቲያን በቤታችን Aለችን? Eነዚህ ሥEላትስ ክርስትናችንን ብሎም Oርቶዶክሳዊነታችንን መግለጽ ይቻላቸዋል? • ለምሳሌ በመለኮታዊ ኃይሉ ሲገለጥ ማንም ሊያየው የማይቻለው የEግዚAብሔር Aብ፣ የEግዚAብሔር ቅ ች ኛ ትወልድ፣ የEግዚAብሔር መንፈስ ቅዱስ ሥEል በቤታችን ይገኛል? ምስጢረ ቁርባን የተመሠረተበትና የተፈጸመበት የምሴተ ሐሙስ ሥEልስ? ማቴ 17፣ ማቴ 3፣ ማቴ 26፡፡ • በመዝ 44፡9፡፡ ‹‹በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።›› በማለት Eንደተጻፈልን Eመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታችን በቀኝ በኩል ሆና Eንደታቀፈችው የምትታይበት ሥEልስ በቤታችን Aለን? በቤታችን በምንሰቅላቸው ሥEላት ላይ ታላቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ይገባናል • የተወደዳችሁ የEግዚAብሔር ቤተሰቦች! Aሁን የትኞቹ ሥEላት Eንደሚገኙ ለመመልከት ወደ Oርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ቤት በመግባት ቅኝት Eናደርጋለን፡፡
  • 6. Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን • ወደ Oርቶዶክሳውያን ቤት ስንገባ ክፉ ሁሉ ወደ ቤቱ Eንዳይቀርብ፣ ቤቱም ቤተ ክርስቲያን ሆና• ወደ Oርቶዶክሳውያን ቤት ስንገባ ክፉ ሁሉ ወደ ቤቱ Eንዳይቀርብ፣ ቤቱም ቤተ ክርስቲያን ሆና የጌታችን ፈቃዱ Eንዲፈጸምባትና ደስ Eንዲሰኝባት በመግቢያው ላይ የሊቀ መላEክት ቅዱስ ሚካኤል ሥEል የቤቱ ጠባቂ ይሆን ዘንድ ተሰቅሎ ልንመለከት Eንችላለን፡፡ መዝ 33፡7-8፡፣ማቴ 18፡10፡፡ • የመላEክት Aለቃ ቅዱስ ሚካኤል ጌታችን Aምላካችን Iየሱስ ክርስቶስ የሚገባባትንና ከAመኑበት Oርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ጋር የሚኖርባትን ቤት የመግቢያ በር ይጠብቃታል፡፡ በቤቱ መግቢያ ላይ • ‹‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።›› ማቴ 11፡28፡፡ በማለት Eንደሚጣራ ሆኖ Eጆቹን ዘርግቶ የተሰቀለውን የጌታችን Aምላካችን Iየሱስ ክርስቶስን ሥEል ልናገኝ Eንችላላን፡፡ • ይህም ሥEል ወደዚህ ቤት የሚገቡትን ሁሉ ችግር፣ ሸክምና ፈተና በራሱ በማኖር ሰላምን ይሰጣቸው• ይህም ሥEል ወደዚህ ቤት የሚገቡትን ሁሉ ችግር፣ ሸክምና ፈተና በራሱ በማኖር ሰላምን ይሰጣቸው ዘንድ ይጋብዛቸዋል፡፡ ገላ 3፡1፡፡ • በተጨማሪም በዚሁ ቤት መግቢያ ላይ በስደቱ የግብጽና የIትዮጵያን ሰዎች የባረከበትን የስደቱን ሥEል ልናገኝ Eንችላለን፡፡ • ይህን ሥEል በቤታችን መግቢያ ላይ ማድረጋችን ጌታችን ከEመቤታችንና ከቅዱስ ዮሴፍ ጋር Eንዲባርከን ያደርገናል፡፡ Iሳ 19፡25፣ Eንባ 3፡7፡፡ • Eንግዲህ ይህን በማድረግ የጌታችን የAምላካችንን በረከት ከEናቱ ከEመቤታችንና ከቅዱሳኑ ጋር ወደምንቀበልበትና ሰላም ወደሞላበት ቤታችን Eንግባ፡፡
  • 7. Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን በማረፊያ ክፍል (Living Room) • ጌታችን በተራራው ስብከት ሲያስተምር የሚያመለክተውን ሥEል ልናደርግ Eንችላላን፡፡ ማቴ 5 - 8፡፡ • ይህንም ሥEል ስንመለከት የጌታችንን ቃሉን Eያስታወስን (Eያሰብን) ሰውነታችንንም Eየተቆታጠርን ሕይወታችንንም የቃሉ ምስክርነት የሚሰጥበት ልናደርገው Eንችላለን፡፡ ይህን ቦታ ቤተሰቡ ሁሉ ከEንግዶቻቸው ጋር የሚሰባሰቡበትና ስለ Aምላካችን ትEዛዛት የሚነጋገሩበት• ይህን ቦታ ቤተሰቡ ሁሉ ከEንግዶቻቸው ጋር የሚሰባሰቡበትና ስለ Aምላካችን ትEዛዛት የሚነጋገሩበት ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ በማEድ ቤት • ጌታችን Aምላካችን በAምስት Eንጀራና በሁለት ዓሣ Aምስት ሺህ ሕዝብ መግቦ ያትረፈረፈበት ሥEል ሊኖር ይችላል፡፡ ማቴ 14፡14-22፡፡ • ይህን ሥEል ስንመለከት ያለን ሀብትና የክፍፍሉ Aለመመጣጠን ወይም ማነስ የማይገድበውን ሁሉን Aትረፍርፎ የሚሰጠውን የጌታችንን በረከቱን (ስጦታውን) Eናስተውላለን፡፡ • ወላጆች ጌታችን ሕዝቡን ከመመገቡ በፊት ስለዘላለማዊቱ መንግሥት ስለመንግስተ ሰማያት በማስተማር ከሥጋ ፍላጎታቸው በፊት መንፈሳዊውን ያሚላ መሆኑን ልብ ማለት ይገባቸዋል፡፡በማስተማር ከሥጋ ፍላጎታቸው በፊት መንፈሳዊውን ያሚላ መሆኑን ልብ ማለት ይገባቸዋል፡፡ • በዚህም መሠረት ለልጆቼ መንፈሳዊ ፍላጎታቸውን Eያሚላሁላቸው ነው ወይስ ሐሳብ ብቻ የማመላልስ ነኝ? ብሎ ራስን መጠየቅም ያስፈልጋል፡፡ • ወላጆች ከቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች Eያነበብን ያነበብነውንም ትርጉም ተምረን በመረዳት ለልጆቻችን Eንደ ሥጋዊ ምግባቸው መንፈሳዊ ምግባቸውን Eናዘጋጅላቸዋለን?
  • 8. Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን • በማEድ ቤታችን ከዚሁ በተጨማሪ የማርታና የማርያም ሥEል ሊኖረን ይችላል፡፡ ሉቃስ 10፡38-42፡፡ Eል ስ ለከት ታች ታ ት ሽ ት ሽ• ይህን ሥEል ስንመለከት ጌታችን ማርታን ‹‹ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።፡፡›› ሉቃ 10፡41-42፡፡ በማለት የነገራትን ቃሉን Eናስታውሳለን፡፡ • ወላጆችም ይህን Aቅጣጫ በመከተል ማንኛውንም ነገር ከማድረጋቸው በፊት ማርያም Eንዳደረገችው ከጌታችን Eግር ሥር በመቀመጥ ከEግዚAብሔር ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ማጥበቅና በጥልቅ መሠረት ላይ ማነጽ ይገባቸዋል፡፡ላይ ማነጽ ይገባቸዋል፡፡ • ወላጆች በዚህ ዘመን ማርያምንም ማርታንም ሆነው መገኘታቸው Eጅግ Aስፈላጊ ነው፡፡ በመመገቢያ ክፍላችን (Dinning Room) • Oርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የመመገቢያ ክፍላችንን በፍራፍሬዎችና በAበቦች ከማድመቅ ይልቅ ‹‹የሚበላኝ ደግሞ ከEኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።›› ዮሐ 6፡57፡፡ ያለውንና የሕይወት Eንጀራ የሆነውን ጌታችን Aምላካችንን የምናስብበት የምሴተ ሐሙስ ሥEል ብናደርግ መልካም ነው፡፡ • ይህን ሥEል ስንመለከት ከቅዱስ ቁርባን መራቃችንን ልናስታውስ Eንችላለን፡፡ • በተጨማሪም በሥEሉ የሚገኘውን ይሁዳን ስንመለከት ኃጢAታችን ከቅዱስ ቁርባን ምን ያህል Eንዳራቀንና ከቅዱሳንም Aንድነት Eንደለየን Eናስተውላለን፡፡Eንዳራቀንና ከቅዱሳንም Aንድነት Eንደለየን Eናስተውላለን፡፡ • Eየተመገብን ሥEሉን መመልከታችን ልባችንም መንፈሳዊውን ምግብ Eንዲመገብ ምክንያት ይሆነዋል
  • 9. Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን የባለትዳሮች የመኝታ ክፍል • በቃና ዘገሊላ ተገኝቶ ጋብቻን የባረከ የጌታችን ሥEል ሊኖር ይችላል፡፡ ዮሐ 2፡1-11፡፡ • የሥEሉ መኖር ጌታችን ከEናቱ ከEመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በሠርግ ቤቱ ተገኝቶ ጋብቻውን Eንደባረከ በዚህም ቤት በመካከላቸው ተገኝቶ ሐሳባቸውን Eንደባረከላቸውና በፍቅርም Eንዳስተሳሰራቸው Eንዲሰማቸው፣ Eንዲረዱ Eንዲያስተውሉ ይረዳል፡፡Eንደባረከላቸውና በፍቅርም Eንዳስተሳሰራቸው Eንዲሰማቸው፣ Eንዲረዱ Eንዲያስተውሉ ይረዳል፡፡ በልጆቻችን ክፍል • በልጆች ክፍል ውስጥ ብዙ ጊዜ ሚኪ ማውስን (Mickey Mouse) የመሳሰሉ የEንስሳትና የAEዋፋት ሥEሎች (ፎቶዎች) Eናገኛለን፡፡ • የOርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ቤት ግን ከልጆቹ Aልጋ በላይ የሚጠብቋቸው መላEክት ሥEል በሌላኛው በኩል በሚገኘው ግድግዳ ላይ ደግሞ ሕጻናትን የሚወዳቸውና ያቀፋቸው በሕጻናት የተከበበው የጌታችን ሥEል ይኖራል፡፡ ማቴ 19፡13-15፣ ማቴ 18፡1-10፡፡ • በተጨማሪም በከብቶች ግርግም የተወለደው የጌታችንንና በሕጻንነቱ ሰማEት የሆነው የቅዱስ ቂርቆስ ሥEላት በልጆች ክፍል ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ማቴ 2፣ Eብ 12፡1 3፡፡ሥEላት በልጆች ክፍል ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ማቴ 2፣ Eብ 12፡1-3፡፡ • ይህም ጎዳናቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ለጌታችን ለAምላካችንና ለቅዱሳኑም ቅርቦች ሆነው መንፈሳዊውን ዓለም በAግባቡ Eየተረዱና መንፈሳዊነቱም Eየተዋሃዳቸው Eንዲያድጉ ይረዳቸዋል፡፡ • የተወደዳችሁ ምEመናን! የOርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ቤት በቅዱሳን ሥEላት ብቻ ሳይሆን በተለያየ ቅርጽ በተሠሩ መስቀሎችም ጭምር የተባረከ ነው፡፡ ገላ 6፡14፣ ፊል 3፡18-21፡፡
  • 10. Oርቶዶክሳዊ ቤተሰብ - በቤታችን ያለች ቤተ ክርስቲያን • ተፈጥሮን የሚያደንቁና የሚወዱም በመዝ 91(92)፡12 ‹‹ጻድቅ Eንደ ዘንባባ ያፈራል፥ Eንደ ሊባኖስ ዝግባም ል E ለ ሳ ጎ ለ ት Aቸ ዘ Eላት ሊያድጋል።›› Eንደተባለው ወደ መንፈሳዊ ጎዳና ለማምራት የሚረዱAቸውን የዘንባባ… ሥEላት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ • ዘንባባ ግንዱ ቢታይም ሥሩ ግን Aይታይም፡፡ ለግንዱ ሕይወቱ ሥሩ ነው፡፡ በዚሁ ዛፍ ሥEል Aማካኝነት የማይታየው EግዚAብሔር የሚታየውን ሰው ከፍጥረታት ሁሉ Aልቆ ሲመግበውና ሲያበረታው የሚኖር መሆኑን Eንማርበታለን፡፡ • የዘንባባ ዛፍ ግንድ ውስጣዊ Aካሉ ነጭ መሆኑ ‹‹ ክፉውን በመልካም Aሸንፍ Eንጂ በክፉ Aትሸነፍ።›› ሮሜ 12፡21፡፡ የተባለውንና በዚህም Eየተመራ የሚኖረውን የጻድቁን ሰው የልብ ንጽሕና ያመለክተናል፡፡ • የዘንባባ ዛፍ ድንጋይ ሲወረውሩበት ወይም ሲያወዛውዙት ፍሬውን Eንደሚያራግፍ ሁሉ ጻድቅ ሰውም ቅዱስ Eስጢፋኖስ ‹‹ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢAት Aትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።›› የሐዋ 7፡60፡፡ በማለት Eንዳደረገው ቅዱሳን በጭቃኔና በግፍ ለሚፈታተኑAቸው ሁሉ የሚጸልዩላቸው መሆኑን Eንማርበታለን፡፡ • በመዝ 18(19)፡1፡፡ ‹‹ሰማያት የEግዚAብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የEጁን ሥራ ያወራል።›› በማለት መዝሙረኛው ዳዊት Eንደዘመረው የEግዚAብሔርን ድንቅ ሥራ ለማሰብ ይረዳን ዘንድዊ ዚ ይ የከዋክብትና የጨረቃም ሥEላት በቤታችን ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ • የEግዚAብሔር ቤተሰቦች! የሰው ወገኖች በጎበኟችሁ ጊዜ ሁሉ በቤታችሁ የምትገኘውን ቤተ ክርስቲያን ሊያገኟት ሊመለከቷት ይችሉ ይሆን? ቤተሰቡ ሁሉ የሚጠቀምባቸውን መንፈሳውያን ሥEላትስ ይመለከቱሊያገኟት ሊመለከቷት ይችሉ ይሆን? ቤተሰቡ ሁሉ የሚጠቀምባቸውን መንፈሳውያን ሥEላትስ ይመለከቱ ይሆን? … ይቆየን፡፡